ተጽናና (Tetsnana) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

መከራው ፡ በዝቶ ፡ ዛሬማ ፡ ጭንቅ ፡ ሆኖብሃል
ሚያዝ ፡ ሚጨበጥ ፡ ከፊትህ ፡ ሁሉ ፡ ርቆሃል
ተስፋ ፡ በመቁረጥ ፡ በርህን ፡ ዘግተህ ፡ ተቀምጠህ
አበቃ ፡ የእኔማ ፡ ነገር ፡ ብልህ ፡ ደምድመህ
ዜናው ፡ ዜናው ፡ ተሰማ
የፍቅር ፡ አምላክ ፡ አለና ፡ ወገን ፡ ተጽናና

አዝ፦ የመጽናናት ፡ አባት ፡ የርህራሄ ፡ አምላክ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነው
ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነው
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)

ስለዚህ ፡ ወንድሜ ፡ ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ ተጽናና
ኢየሱስ ፡ አለና (፬x)
ኢየሱስ ፡ አለና (፬x)

ተደግፈኸው ፡ አልጣለህ ፡ እርሱን ፡ ተማምነህ
ተተግተኸው ፡ አልሸሸህ ፡ ደካማ ፡ ሆነህ
ዓይኖቹ ፡ ዛሬም ፡ ያያሉ ፡ ከቶ ፡ አልደከሙም
ሰፊ ፡ ትከሻው ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ይሸከማሉ
አይዞህ ፡ አይዞህ ፡ ተጽናና
ክብርህን ፡ ጥለህ ፡ አምልከው ፡ ላደረገህ ፡ ቀና

አዝ፦ የመጽናናት ፡ አባት ፡ የርህራሄ ፡ አምላክ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነው
ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነው
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)

ስለዚህ ፡ ወንድሜ ፡ ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ ተጽናና
ኢየሱስ ፡ አለና (፬x)
ኢየሱስ ፡ አለና (፬x)

ጌታ ፡ እያለ ፡ የምን ፡ ማዘን ፡ ነው
ለእርሱ ፡ አስረክቦ ፡ እርፍ ፡ ማለት ፡ ነው
ሃዘኔ ፡ ጠፍቶ ፡ እምባዬ ፡ ታብሷል
ሁሉም ፡ አለፈ ፡ አስረስቶኛል
አላዝንም ፡ ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ እኔ (፬x)

ጌታ ፡ እያለ ፡ ከጐኔ
እርሱ ፡ እያለ ፡ ከጐኔ (፬x)