From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሰው ፡ ቢተየቅ ፡ ስለምኞቱ
አለው ፡ ብዙ ፡ የሚናገረው
ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ስለሚጠፋ
ይጨነቃል ፡ ነገን ፡ ሳያውቀው
የእኔ ፡ መሻት ፡ አንድ ፡ ነገር
ስኖር ፡ ሳለሁ ፡ በዚች ፡ ምድር
ሁልጊዜ ፡ እንድኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋር
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልኝ ፡ ፀጋህ
ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልኝ ፡ ፀጋህ
አባቴ ፡ ሆይ ፡ ይብዛልኝ ፡ ፀጋህ
የእኔ ፡ ቦታ ፡ ይሁን ፡ አንተ ፡ ጋር
አድራሻዬ ፡ ከዙፋንህ ፡ ስር
ዛሬም ፡ ፀጋህ ፡ ያግዘኝና
አልታጣም ፡ ሁሌ ፡ ከእግርህ ፡ ስር (፪x)
በምድር ፡ ያለው
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
ምንም ፡ ቢለፋ ፡ ምንም ፡ ቢደከም ፡ ሰው ፡ የለም ፡ ብርቱ
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
በምድር ፡ የሚገኝ ፡ ፍፁም ፡ ያልሆነ ፡ ጊዜያዊ ፡ ደስታ
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
ዕድሜ ፡ የሌለው ፡ እንደ ፡ እንፋሎት ፡ ታይቶ ፡ የሚጠፋ
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ (፪x)
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ (፪x)
አልፈልግም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
አይሆነኝም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
አልመኝም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
አያምረኝም ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ (፪x)
ዘለዓለሜ ፡ ይሁን ፡ አንተ ፡ ጋር
አድራሻዬ ፡ ከዙፋንህ ፡ ስር
ዛሬም ፡ ፀጋህ ፡ ያግዘኝና
አልታጣም ፡ ሁሌ ፡ ከእግርህ ፡ ስር (፪x)
በምድር ፡ ያለው
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
ምንም ፡ ቢለፋ ፡ ምንም ፡ ቢደከም ፡ ሰው ፡ የለም ፡ ብርቱ
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
በምድር ፡ የሚገኝ ፡ ፍፁም ፡ ያልሆነ ፡ ጊዜያዊ ፡ ደስታ
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ
ዕድሜ ፡ የሌለው ፡ እንደ ፡ እንፋሎት ፡ ታይቶ ፡ የሚጠፋ
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ (፪x)
ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ (፪x)
|