ስለበላሁ (Selebelahu) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

አሜን


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ስለበላሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ አልከተልህም ፡ እኔ
ፈቃድህን ፡ እያደረኩ ፡ እኖራለሁ ፡ በዘመኔ (፪x)

አይረሳኝ ፡ ትላንት ፡ ያደረገው
አስገረመኝ ፡ ለካ ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው
አሰናብቶ ፡ ሌላውን ፡ ሲሸኝ
ሊሰራብኝ ፡ እኔን ፡ ግድ/ቆይ ፡ አለኝ (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ የቀመስኩት ፡ እኔስ ፡ በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ነገር ፡ አለ
አንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ (፪x)

ጌታ ፡ አንተን ፡ ብዬ ፡ ስምህን ፡ ጠርቼ
ነገር ፡ የሞላ ፡ ቀን ፡ ስራህን ፡ ሰርቼ
በሆዴ ፡ እንዳልታለል ፡ ሲሞላ ፡ የልቡ ፡ ደርሶ
እንዳይሸሽ ፡ ጥሎ ፡ እንዳይሄድ ፡ ባመጣው ፡ እግሩ ፡ ገስግሶ
አይሆነው ፡ ያለአንተ ፡ ኑሮ ፡ ልቤ ፡ አውቆሃል ፡ ከአምናው ፡ ዘንድሮ

አዝ፦ እኔስ ፡ የቀመስኩት ፡ እኔስ ፡ በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ነገር ፡ አለ
አንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ (፪x)

ወስኜ ፡ ተነሳሁ ፡ ልከተልህ ፡ አንተን
ወደ ፡ ኋላ ፡ ትቼው ፡ የራሴን ፡ ነገሬን
አንተው ፡ ጋር ፡ ይሻለኛል ፡ ቢሞላም ፡ ቢጐድልም ፡ ሁሉ
ከደጅህ ፡ የትም ፡ አልሄድም ፡ እቤትህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሙሉ
ደግ ፡ ነህ ፡ እጅህ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ዘመኔ ፡ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ ነው

አዝ፦ እኔስ ፡ የቀመስኩት ፡ እኔስ ፡ በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ነገር ፡ አለ
አንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ (፪x)