ኑርለት (Nurelet) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

እንደልቡ ፡ ሃሳብህን ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ፈቃዱ
ለእርሱ ፡ የተለዩለት ፡ ለአንዱ ፡ ለሰገዱ
መስለውት ፡ በመኖር ፡ ጌታን ፡ ላስከበሩ
ዋጋ ፡ አለ ፡ ከእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ሲመጣ ፡ በክብሩ

ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ አስብ ፡ አስተውል
በዚህች ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ እንዳትታለል
አንድ ፡ ቀን ፡ ወደላይ ፡ በክብር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር
ስትሄድ ፡ በደመና ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ የሁልጊዜ ፡ እረፍት
ሃዘን ፡ በሌለበት ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ገነት
ትኖራለህ ፡ በዚያች ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ
ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ተስማማ

ኑርለት ፡ ኑርለት ፡ ለጌታ
ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደሃሳቡ
ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደፈቃዱ
ያን ፡ ጊዜ ፡ ታያለህ
እርሱ ፡ አንተን ፡ መውደዱ

እንደፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አስተምረኝ
ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ
ለፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖረን ፡ አስተምረኝ
ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ

ልኑር (፪x) ፡ ልኑር (፪x)
እንደ ፡ ፈቃድህ ፡ ልኑር
እንደ ፡ ሃሳብህ ፡ ልኑር
ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ጉልበት ፡ ስጠኝ
እኔ ፡ አልችልም ፡ ባክህ ፡ አግዘኝ (፪x)

አውቀህ ፡ አገልግለህ ፡ አምላክህን ፡ በክብር
ሚገባውን ፡ መጽዋት ፡ አቅርብ ፡ ከእግሩ ፡ ስር
ከቶ ፡ እንዳትሰማ ፡ የጠላትን ፡ ወሬ
ክብርህ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ አስተውል ፡ ወገኔ

ለአፍታ ፡ እንዳትዘነጋ ፡ የመቆምህን ፡ ሚስጥር
ዛሬን ፡ የማየትህ ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእግዚአብሔር
ክብርና ፡ ዝና ፡ ሃብት ፡ ስላለህ ፡ ሳይሆን
ስለመረጠህ ፡ ሰው ፡ ስለለየህ ፡ አንተን (፪x)

ኑርለት ፡ ኑርለት ፡ ለጌታ
ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደሃሳቡ
ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደፈቃዱ
ያን ፡ ጊዜ ፡ ታያለህ
እርሱ ፡ አንተን ፡ መውደዱ

እንደፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አስተምረኝ
ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ
ለፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖረን ፡ አስተምረኝ
ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ

ልኑር (፪x) ፡ ልኑር (፪x)
እንደ ፡ ፈቃድህ ፡ ልኑር
እንደ ፡ ሃሳብህ ፡ ልኑር
ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ጉልበት ፡ ስጠኝ
እኔ ፡ አልችልም ፡ ባክህ ፡ አግዘኝ (፪x)