ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን (Nu Des Yebelen) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:18
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አዝአለ ፡ እንደገዛ ፡ አለ ፡ እንደከበረ (፪x)
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ያምልከው
ይገባዋል ፡ እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነው
ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን ፡ በእርሱ
ሃሴት ፡ እንዳድርግ ፡ በንጉሡ (፪x)

ኑ ፡ ደስ ፡ ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ለእግዚአብሔር ፡ እንዘምር (፬x)

ለመድሃኒታችን ፡ ዕልል ፡ እንበል
በምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ ዘወትር ፡ እንቅረብ
በዝማሬ ፡ እና ፡ በዕልልታ ፡ ሆታ
ታላቅ ፡ እናድርገው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ለእግዚአብሔር ፡ እንዘምር (፬x)

የምድር ፡ ጥልቁቆች ፡ በእጁ ፡ ናቸው
የተራራ ፡ ጫፎችም ፡ የእርሱ ፡ ናቸው
እርሱ ፡ ፈጥሯታልና ፡ ባሕር ፡ የእርሱ ፡ ናት
እጁ ፡ የብስን ፡ አበጀ ፡ እጁ ፡ እኔን ፡ አበጀ
የበላይነቱን ፡ ፍጥረት ፡ አወጀ (፪x)

አዝአለ ፡ እንደገዛ ፡ አለ ፡ እንደከበረ (፪x)
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ያምልከው
ይገባዋል ፡ እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነው
ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን ፡ በእርሱ
ሃሴት ፡ እንዳድርግ ፡ በንጉሡ

ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ለእግዚአብሔር ፡ እንዘምር (፬x)

የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ጣኦታት ፡ ናቸው
ሁሉ ፡ ነገር ፡ ያላቸው ፡ ግን ፡ የሌላቸው
የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ሰማይን ፡ ሰራ
ክብር ፡ ይኸው ፡ በፊቱ ፡ ሞገስ ፡ ይኸው ፡ በፊቱ
በመቅደሱ ፡ ውስጥ ፡ አለ ፡ ውበቱ (፪x)

አዝኑ ፡ ደስ ፡ ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ለእግዚአብሔር ፡ እንዘምር (፬x)
ለመድሃኒታችን ፡ ዕልል ፡ እንበል
በምሥጋና ፡ ፊቱ ፡ ዘወትር ፡ እንቅረብ
በዝማሬ ፡ እና ፡ በዕልልታ ፡ ሆታ
ታላቅ ፡ እናድርገው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

ኑ ፡ ደስ ፡ ይበለን
ለእግዚአብሔር ፡ እንዘምር (፰x)