ፊትህን ፡ ሳይ (Fitehen Say) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ፊትህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ
ፊትህን ፡ ሳይ ፡ እጽናናለሁ ፡ እኔ ፡ እጽናናለሁ
ፊትህን ፡ ሳይ ፡ እበረታለሁ
ወደአንተ ፡ መጥቼ ፡ ሁሉነረሳለሁ
እምባዬ ፡ ታብሶ ፡ ደስታን ፡ እሞላለሁ (፪x)

እራሴን ፡ ሳየው ፡ ማንነቴን ፡ ሳውቀው
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ምንም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ
አዝኜ ፡ መጥቼ ፡ ስቄ ፡ እመለሳለሁ
ቀና ፡ ብዬ ፡ ሳይህ ፡ ፊትህ ፡ ጠጋ ፡ እላለሁ (፪x)

የመጽናኛዬ ፡ ቦታው ፡ የለቅሶ ፡ ሃዘኔ ፡ መርሻው
ፊትህ ፡ ነው (፫x) ፡ ደስ ፡ የሚያሰኘው
ፊትህ ፡ ነው (፫x) ፡ ደስ ፡ የሚያሰኘው (፪x)

ሌላ ፡ እኔ ፡ አልሻም ፡ የልብ ፡ የሚሆን ፡ የለም
ሁሉም ፡ አላፊ ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ ጠፊ
ፊቴን ፡ መልሻለሁ ፡ አይጠቅመኝም ፡ ሌላ
አንተኑን ፡ መመልከት ፡ ያዋጣኛልና (፪x)

የመጽናኛዬ ፡ ቦታው ፡ የለቅሶ ፡ ሃዘኔ ፡ መርሻው
ፊትህ ፡ ነው (፫x) ፡ ደስ ፡ የሚያሰኘው
ፊትህ ፡ ነው (፫x) ፡ ደስ ፡ የሚያሰኘው (፪x)