በጐነቴ (Begonetie) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ከአንተ ፡ በቀር ፡ በጐነት ፡ የለኝም ፡ ከአንተ ፡ በቀር
ከአንተ ፡ በቀር ፡ መመኪያም ፡ የለኝም ፡ ከአንተ ፡ በቀር (፪x)

ተስፋ ፡ ማደርገው ፡ አለኝ ፡ የምለው
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተኑ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
አንተኑ ፡ ብቻ ፡ ነው (፬x)

ዓሣ ከውኃ ፡ ውስጥ ፡ ሲወጣ
ከቶ ፡ እንደሌለው ፡ የመኖር ፡ ተስፋ
እኔም ፡ ያለአንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም
ነፍሴ/ልቤ ፡ ወደደህ ፡ አልለይህም (፪x)

በጐነቴ (፬x) ፡ አለቴ ፡ መድሃኒቴ
እወድሃለሁ ፡ ጉልበቴ
እወድሃለሁ ፡ ጉልበቴ (፬x)

ስገረምና ፡ ስደነቅ ፡ ሁሌ
በአንተ ፡ ቤት ፡ ይለቅ ፡ ጌታ ፡ ዘመኔ
ደግ ፡ እንዳንተማ ፡ አይቼ ፡ አላውቅም
ሁሌ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ አትለወጥም (፪x)

ተስፋ ፡ ማደርገው ፡ አለኝ ፡ የምለው
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተኑ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
አንተኑ ፡ ብቻ ፡ ነው (፬x)