አላለቅስም (Alaleqsem) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 4.jpg


(4)

ሰው ፡ ቢጠየቅ
(Sew Biteyeq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:04
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ዛሬም ፡ ለቅሶ ፡ ዋይታ ፡ ዋይታ
የዚህ ፡ ምድር ፡ ኑሮ ፡ የለውም ፡ እርካታ
ጊዜው ፡ ሲደርስ ፡ ያኔ ፡ መምጫው ፡ የጌታዬ
ፊት ፡ ለፊቴ ፡ ሳየው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ደስታዬ (፪x)

አዝአላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ
የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር
ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x)

ዘለዓለሜ ፡ በዚያ ፡ በክብር
በአብ ፡ ቀኝ ፡ በደስታ ፡ ለመኖር
በእርግጥ ፡ ናፍቄያለሁ ፡ ደርሳለሁ
የታረደውን ፡ በግ ፡ መሲሁን ፡ አያለሁ (፪x)

አዝአላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ
የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር
ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ

በዚህ ፡ ምንም ፡ የለኝ ፡ የለኝ
የሰው ፡ ዓይን ፡ ያላየው ፡ ያላየው
በእጅ ፡ ያልተሰራው ፡ እርስቴ
እንዴት ፡ ያማረ ፡ ነው ፡ የላይኛው ፡ ቤቴ (፪x)

አዝአላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ
የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር
ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ

የፍጥረት ፡ ሩጫ ፡ ሲገታ
ለምድሩ ፡ በጊዜው ፡ ሲያበቃ
ሙሽራው ፡ በድንገት ፡ ሲመጣ
ፍጻሜን ፡ ያገኛል ፡ የቅዱሳን ፡ ተስፋ (፪x)

አዝአላለቅስም ፡ አላለቅስም (፪x)
ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ፡ ከቶ ፡ አልቆርጥም ፡ ተስፋ
የላይኛው ፡ ክብር ፡ ይበልጣል ፡ ከምድር
ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ እፈልጋለሁ (፪x)