ዞር በል አንተ ክፉ (Zor Bel Ante Kifu) - ተመስገን ማርቆስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተመስገን ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ላታደርግ ላትፈፅም
(Lataderg Latfetsem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ዞር ፡ በል ፡ አንተ ፡ ክፉ ፡ ሂድ ፡ ከአጠገቤ
ተራዬን ፡ ልጨርስ ፡ ልድረስ ፡ እስከግቤ (፪x)
ጌታ ፡ ያየልኝንም ፡ ሄጄ ፡ እስክወርሰው
መቆም ፡ አልፈልግም ፡ ልሂድ ፡ ላገልግለው (፪x)

አላለቀም ፡ ገና ፡ በእኔ ፡ የጀመረው
አላለቀም ፡ ገና ፡ በእኔ ፡ የጀመረው
ገለል ፡ በል ፡ ከፊቴ ፡ ጌታን ፡ ላገልግለው
ጌታን ፡ ለጌልግለው (፪x)

በእኔ ፡ የጀመረውን ፡ ሳይፈጽም ፡ አይቀርም
ታማኝ ፡ ነው ፡ በቃሉ ፡ ጌታ ፡ አይረሳኝም
እንቅፋት ፡ ልትሆኑ ፡ ገና ፡ ከጅምሩ
ቅባቱ ፡ እንዳይወጣ ፡ ይዛቹህ ፡ ልታስሩ
አላማዬ ፡ ግቤ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለእኔ
አጠገቤ ፡ እትምጡ ፡ ዞርበሉ ፡ ከጐኔ

አዝ፦ ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x)
ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና
ይጨምራል ፡ ገና
ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x)
ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና
ይጨምራል ፡ ገና
ይጨምራል ፡ ገና (፬x)

ገና ፡ እጓዛለሁ ፡ አምላኬን ፡ ታምኜ
አብሬው ፡ ዞራለሁ ፡ ትከሻው ፡ ላይ ፡ ሆኜ
ከእንግዲህ ፡ ላትደፍሩ ፡ ሂዱ ፡ ከዚህ ፡ በቃ
አምላክ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ የሁሉም ፡ አለቃ
እርሱ ፡ ቀኜን ፡ ይዟል ፡ ፈጽሞ ፡ ላይለቀኝ
እከተለዋለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ሚያዋጣኝ

አዝ፦ ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x)
ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና
ይጨምራል ፡ ገና
ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x)
ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና
ይጨምራል ፡ ገና
ይጨምራል ፡ ገና (፬x)

ብላቴና ፡ እያለሁ ፡ በትንሽነቴ
ወንድሞቼን ፡ መርጦ ፡ ረስቶኝ ፡ ሳል ፡ አባቴ
አምላኬ ፡ አስጠርቶኝ ፡ ቅባት ፡ ፈሶብኛል
ለተለየ ፡ አላማው ፡ እኔን ፡ ፈልጐኛል
ስሙን ፡ ማን ፡ ነው ፡ ያሉት ፡ ያ ፡ ያልተገረዘ
የእስራኤልን ፡ ልብ ፡ እንዲህ ፡ የበዘበዘ
ልሂድ ፡ ልጋጠመው ፡ በአምላኬ ፡ ሥም ፡ ልምታው
በላዬ ፡ የፈሰሰው ፡ ሚዘርር ፡ ቅባት ፡ ነው

አዝ፦ ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x)
ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና
ይጨምራል ፡ ገና
ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x)
ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና
ይጨምራል ፡ ገና
ይጨምራል ፡ ገና (፲፪x)