ላታደርግ ላትፈፅም (Lataderg Latfetsem) - ተመስገን ማርቆስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተመስገን ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ላታደርግ ላትፈፅም
(Lataderg Latfetsem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

ላታደርግ ላትፈፅም ቃል አትገባም አንተ
ይሆናል ይሳካል እምነት አለኝ ባንተ (2x)

አላንገራግርም ይሆናልወይ ብዬ
አማራጭ አላይም ቃሉን ወዲያ ጥዬ
አደርጋለሁ ካለኝ ጌታዬን ልመነው
በትዕግስት ልጠብቅ አንድ እሱ በቂ ነው
ጌታዬ በቂ ነው
አዝ....
ላታደርግ ላትፈፅም ቃል አትገባም አንተ
ይሆናል ይሳካል እምነት አለኝ ባንተ (2x)

እኔ አምነዋለሁ ሌላ ሌላ አላይም
ምንም ቢዘገይም መምጣቱ አይቀርም
የተናገረኝን አንድ ቀን ያደርጋል
ላይፈፅም ላይሰራ መቼ ቃል ይገባል
ልመነው ሰርቶ ያሳየኛል
አዝ....
ላታደርግ ላትፈፅም ቃል አትገባም አንተ
ይሆናል ይሳካል እምነት አለኝ ባንተ (2x)

ቃል ያለው ሰው እኮ ነኝ ለምን ቆዝማለሁ
በሆነው ባልሆነው ለምንስ አዝናለሁ
መኖሪያየ ከላይ ሀገሬ በሰማይ
ጊዚያዊ ነኝ በዚህ ቆይታዬ ሲታይ
ቀን አዟል እሱን ሄጀ እንዳይ

ጊዚያዊ ጊዚያዊ ነኝ በዚህ ምድር ላይ
እንግዳ እንግዳ ነኝ በዚህ ምድር ላይ
አንድ ቀን ሁሉ አልፎ ሲሄድ ወደላይ
ደስታዬ አምላኬን ፊትለፊት ሳይ (4x)