አንተ ለኔ መልካም ነህ (Ante Lene Melkam Neh) - ተመስገን ማርቆስ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተመስገን ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ላታደርግ ላትፈፅም
(Lataderg Latfetsem)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

እጄን ፡ ይዘህ ፡ አንተ ፡ ስትመራኝ
ለእራስ ፡ ዓላማ ፡ ስትለየኝ
መልካምነትህን ፡ (ጌታ): ያን ፡ ጊዜ ፡ አየሁ
እንኳን ፡ አየኸኝ ፡ በአንተ ፡ ወግ ፡ አየሁ (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)

ሞቴን ፡ ሲመኘው ፡ ያ ፡ ክፉ ፡ ጠላት
በአንተ ፡ ግን ፡ ዛሬ ፡ አገኘሁ ፡ ሕይወት
ላብዛ ፡ ምሥጋና ፡ ላሰማ ፡ ዜማ
ጠላት ፡ እያየ ፡ ጆሮው ፡ እየሰማ (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)

አልሻም ፡ ሌላ ፡ አንተ ፡ አለህልኝ
መልካም ፡ አሳቢዬ ፡ ወዳጅ ፡ የሆንከኝ
ኮራሁብህ ፡ (በቃ) ፡ አላፍርም ፡ በአንተ
ገላግለኸኛል ፡ ለይተህ ፡ አንተ (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ጌታ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)
ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ለእኔ (፪x)