ስገረም (Segerem) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 2.jpg


(2)

ኃይል ፡ አለ
(Hail Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አየሁ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ የለም
ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም
ወዳጅ ፡ ቢሆን

አዝ፦ ጓዳዬ ፡ ሲሞላ ፡ ስገረም ፡ ኦሆ ፡ ስገረም
ያሰብኩት ፡ ሲሳካ ፡ ስገረም ፡ አሄ ፡ ስገረም
የለመንኩት ፡ ሲሆን ፡ ስገረም ፡ እኔ ፡ ስገረም
አየሁ ፡ ወዳጅ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ አባት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ ውዴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም

ስራዬ ፡ ተሰርቶ ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ አልቆ
በምሥጋና ፡ ሞላኝ ፡ መርገሜን ፡ ወስዶ
ስገረም ፡ ስደነቀኝ ፡ ሚስጥሩ ፡ ሰገባኝ
የጥያቄዬ ፡ መልስ ፡ ጌታዬ ፡ ሆነልኝ

አዝ፦ ጓዳዬ ፡ ሲሞላ ፡ ስገረም ፡ ኦሆ ፡ ስገረም
ያሰብኩት ፡ ሲሳካ ፡ ስገረም ፡ አሄ ፡ ስገረም
የለመንኩት ፡ ሲሆን ፡ ስገረም ፡ እኔ ፡ ስገረም
አየሁ ፡ ወዳጅ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ አባት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ ውዴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም

እጄን ፡ በአፌ ፡ ጭኜ ፡ ዛሬ ፡ እንዳመሰግን
መከራዬን ፡ ድልድይ ፡ አድርጐ ፡ አሻገረኝ
በአለፍኩት ፡ ጐዳና ፡ ከእኔስ ፡ አይለየኝ
ተገረም ፡ ብሎኛል ፡ ይህን ፡ ፀጋ ፡ ሰጥቶኝ

አዝ፦ ጓዳዬ ፡ ሲሞላ ፡ ስገረም ፡ ኦሆ ፡ ስገረም
ያሰብኩት ፡ ሲሳካ ፡ ስገረም ፡ አሄ ፡ ስገረም
የለመንኩት ፡ ሲሆን ፡ ስገረም ፡ እኔ ፡ ስገረም
አየሁ ፡ ወዳጅ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ አባት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ ውዴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም

በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ወደ ፡ አምላኬ ፡ ጮህኩኝ
ማድጋዬን ፡ ሞላው ፡ መጥቶ ፡ አሳረፈኝ
ተደላድልኩ ፡ በቃ ፡ ተሞላ ፡ ጓዳዬ
ተትረፍርፎልኛል ፡ ተከፍሎ ፡ እዳዬ [1]

አዝ፦ ጓዳዬ ፡ ሲሞላ ፡ ስገረም ፡ ኦሆ ፡ ስገረም
ያሰብኩት ፡ ሲሳካ ፡ ስገረም ፡ አሄ ፡ ስገረም
የለመንኩት ፡ ሲሆን ፡ ስገረም ፡ እኔ ፡ ስገረም
አየሁ ፡ ወዳጅ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ አባት ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም
አየሁ ፡ ውዴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የለም

  1. ፪ ነገሥት ፬ ፡ ፩ - ፯ (2 Kings 4:1-7)