ለየት ፡ አድርጐልኛል (Leyet Adergolegnal) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 2.jpg


(2)

ኃይል ፡ አለ
(Hail Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

የአምላኬ ፡ ስራው ፡ ይገርመኛል
የኢየሱሴ ፡ ስራው ፡ ይደንቀኛል
(፪x)
ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ ፈጥሮ ፡ ሠማይን
ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ ፈጥሮ ፡ ምድርን

አዝይገርማል (፫x)
ሥራው ፡ ያስገርማል
ይደንቃል ፡ (ይደንቃል) (፫x)
ሥራው ፡ ያስደንቃል

ይሁን ፡ ብሎ ፡ ከፈጠራቸው
በቃል ፡ ብቻ ፡ እርሱ ፡ ካደረጋቸው
እኔን ፡ ለየት ፡ አድርጐኛል
ጌታዬ ፡ በአምሳሉ ፡ ፈጥሮኛሉ
(፪x)

ይሁን ፡ ብሎ ፡ ከፈጠራቸው
በቃል ፡ ብቻ ፡ እርሱ ፡ ካዘዛቸው
እኔን ፡ ለየት ፡ አድርጐኛል
ጌታዬ ፡ በአምሳሉ ፡ ፈጥሮኛሉ
(፪x)

ፍጥረትን ፡ ሲፈጥር ፡ የሚገርመኝ ፡ ለእኔ
ሠማይ ፡ ይሁን ፡ አለ ፡ ሁነ ፡ ድሮ ፡ ያኔ
ይሁን ፡ ከተባለው ፡ ለየት ፡ አድር
እርሱን ፡ የምመስል ፡ ውብ ፡ አድርጐ ፡ ሰርቶኛል
ገዢ ፡ አደረገኝ ፡ በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ
የበላይ ፡ እንድሆን ፡ ትዛዝ ፡ ሰጠኝ ፡ ከላይ
ልዩ ፡ ሰው ፡ አድርጐ ፡ በምድር ፡ አስቀመጠኝ
ይሁን ፡ ብሎ ፡ ሳይሆን ፡ በእጆቹ ፡ ሰራኝ

አዝይገርማል (፫x)
ሥራው ፡ ያስገርማል
ይደንቃል ፡ (ይደንቃል) (፫x)
ሥራው ፡ ያስደንቃል

የአምላኬ ፡ ስራው ፡ እኔስ ፡ ይደንቀኛል
ከአፉ ፡ የሚወጣው ፡ ቃል ፡ አስገርሞኛል
ቃል ፡ ተናግሮ ፡ ብቻ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አረገ
እኔን ፡ በእራሱ ፡ አምሳል ፡ ቀርጾኝ
ለየት ፡ አደረገ

የአምላኬ ፡ ስራው ፡ ይገርመኛል
የኢየሱሴ ፡ ስራው ፡ ይደንቀኛል
(፪x)
ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ ፈጥሮ ፡ ሠማይን
ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ ፈጥሮ ፡ ምድርን

አዝይገርማል (፫x)
ሥራው ፡ ያስገርማል
ይደንቃል ፡ (ይደንቃል) (፫x)
ሥራው ፡ ያስደንቃል

ይሁን ፡ ብሎ ፡ ከፈጠራቸው
በቃል ፡ ብቻ ፡ እርሱ ፡ ካዘዛቸው
እኔን ፡ ለየት ፡ አድርጐኛል
ጌታዬ ፡ በአምሳሉ ፡ ፈጥሮኛሉ
(፪x)