እፎይ (Efoy) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 2.jpg


(2)

ኃይል ፡ አለ
(Hail Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፫x)
የእራሴ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፫x)
ወዳጅ ፡ የሚሏቸው ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲለዩ
የቅርቤ ፡ ያልኳቸው ፡ ከአንተ ፡ ሰስተያዩ

ግን ፡ አንተ ፡ ጥለህ ፡ የማትሄድ
የማትከዳ ፡ አብዝተህ ፡ የምትወድ
ወዳጄ ፡ ብዬ ፡ የማላፍርብህ
አንተን ፡ ነው ፡ የእራሴ ፡ ያረኩህ (፪x)

የእራሴ ፡ አልኩኝ ፡ ጉያህ ፡ ሥር ፡ ሆኜ
አንዳች ፡ ላይነካኝ ፡ በአንተ ፡ ታምኜ
የግሌን ፡ ወዳጅ ፡ ማን ፡ ሊወስድብኝ
ሌላውን ፡ ትቼ ፡ ስሩ ፡ ገባሁኝ
የእራሴ ፡ አልኩኝ

የእራሴ ፡ የእራሴ ፡ የእራሴ
የግሌ ፡ የግሌ ፡ የግሌ

አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፫x)
የእራሴ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፫x)
ወዳጅ ፡ የሚሏቸው ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲለዩ
የቅርቤ ፡ ያልኳቸው ፡ ከአንተ ፡ ሰስተያዩ

ግን ፡ አንተ ፡ ጥለህ ፡ የማትሄድ
የማትከዳ ፡ አብዝተህ ፡ የምትወድ
ወዳጄ ፡ ብዬ ፡ የማላፍርብህ
አንተን ፡ ነው ፡ የእራሴ ፡ ያረኩህ (፪x)

ከእንግዲህ ፡ አልፈራም ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ
የያዝኩት ፡ ታማኝ ፡ ሆኖኝ ፡ ጋሻዬ
ጥሎኝ ፡ አልሄድም ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ትቶ
ና ፡ ልጄ ፡ እያለ ፡ እጄን ፡ ጐትቶ
አስገባኝ ፡ ቀቶ

አስገባኝ ፡ አስገባኝ ፡ አስገባኝ
አስጠጋኝ ፡ አስጠጋኝ ፡ አስጠጋኝ

ተደላደልኩኝ ፡ ወዳጅ ፡ አገኘሁ
እፎይ ፡ የሚያስብል ፡ የሚመች ፡ ነው
ጊዜ ፡ አይቶ ፡ አይርቅም ፡ ሁልጌዜ ፡ ያው ፡ ነው
ስጋት ፡ አይገባኝ ፡ ልቤ ፡ ሙሉ ፡ ነው
እፎይ ፡ ብያለሁ

እፎዪ ፡ እፎዪ ፡ እፎዪ ፡ እፎይ (፪x)

አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፫x)
የእራሴ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፫x)
ወዳጅ ፡ የሚሏቸው ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲለዩ
የቅርቤ ፡ ያልኳቸው ፡ ከአንተ ፡ ሰስተያዩ

ግን ፡ አንተ ፡ ጥለህ ፡ የማትሄድ
የማትከዳ ፡ አብዝተህ ፡ የምትወድ
ወዳጄ ፡ ብዬ ፡ የማላፍርብህ
አንተን ፡ ነው ፡ የእራሴ ፡ ያረኩህ (፪x)