በጨነቀኝ ፡ ጊዜ (Becheneqegn Gizie) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 2.jpg


(2)

ኃይል ፡ አለ
(Hail Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ፀሎቴ
በእንባ ፡ ስነግርህ ፡ ጭንቀቴን
ለካስ ፡ ሰምተኸኛል ፡ ተመሥገን
ነዶ ፡ አስታቀፍከኝ ፡ ያማረውን

አዝ፦ በዚያ ፡ በጣር ፡ ጊዜ ፡ ለሰማኸኝ
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ለመራኸኝ
ይሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ምሥጋናዬ
ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፪x)

ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፬x)

ሁሉ ፡ አልፎ ፡ ዛሬ ፡ ዘምራለሁ
የቃርሚያውን ፡ ሕይወት ፡ አልፌያለሁ
እልፍ ፡ አደረገኝ ፡ አከበረኝ
በአምላኬ ፡ ከፍታን ፡ አገኘሁኝ

አዝ፦ በዚያ ፡ በጣር ፡ ጊዜ ፡ ለሰማኸኝ
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ለመራኸኝ
ይሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ምሥጋናዬ
ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፪x)

እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ነግቶልኛል
ከአምላኬ ፡ ጉብኝት ፡ ሆኖልኛል
የጨለማው ፡ ዘመን ፡ አለፈና
ልዘምር ፡ በቃሁኝ ፡ አልኩኝ ፡ ቀና

አዝ፦ በዚያ ፡ በጣር ፡ ጊዜ ፡ ለሰማኸኝ
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ለመራኸኝ
ይሰዋ ፡ በፊትህ ፡ ምሥጋናዬ
ሰምሮልኝ ፡ አየሁኝ ፡ በአንተ ፡ ኑሮዬ (፪x)