አንደኛ (Andegna) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 2.jpg


(2)

ኃይል ፡ አለ
(Hail Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ግሩም
ሊዘራ ፡ ሲነሳ ፡ አንዳች ፡ አያግደውም
ባለ ፡ ብዙ ፡ ግርማ ፡ አሃ
ባለ ፡ ብዙ ፡ ዝና ፡ አሃ

እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
ኃይልህ ፡ የበረታ
ሁሌ ፡ ድል ፡ ነሺ ፡ ነህ
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ
አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ

አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ (፬x)
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ (፪x)

ጌታዬ ፡ ስትሰራ ፡ የሚያግድህ ፡ የለ
አማካሪ ፡ ሳይኖር ፡ ሁሉን ፡ ታደርጋለህ
በኃይል ፡ በችሎትህ ፡ አንተ ፡ የበረታህ
አቅምህ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ መቼም ፡ አትረታ
ድል ፡ ነሽ ፡ አንደኛ ፡ አንተ ፡ የሁሉ ፡ ዳኛ (፪x)

አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ግሩም
ሊዘራ ፡ ሲነሳ ፡ አንዳች ፡ አያግደውም
ባለ ፡ ብዙ ፡ ግርማ ፡ አሃ
ባለ ፡ ብዙ ፡ ዝና ፡ አሃ

እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
ኃይልህ ፡ የበረታ
ሁሌ ፡ ድል ፡ ነሺ ፡ ነህ
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ
አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ

አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ (፬x)
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ (፪x)

የሠማይ ፡ አንደኛ ፡ የምድር ፡ አንደኛ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ብቸኛ (፪x)

በእኔ ፡ ልትጠቀም ፡ በእኔ ፡ ልትሰራ
ነጥቀህ ፡ አወጣኸኝ ፡ ከዚያ ፡ ባለጋራ
አዲስ ፡ ጉዞ ፡ ጀመርኩ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ወደፊት
ትንሳኤ ፡ ሆነልኝ ፡ ሞቴ ፡ ወደ ፡ ሕይወት
ገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ እኔ ፡ የአንተ ፡ መሆኔ (፪x)

አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ግሩም
ሊዘራ ፡ ሲነሳ ፡ አንዳች ፡ አያግደውም
ባለ ፡ ብዙ ፡ ግርማ ፡ አሃ
ባለ ፡ ብዙ ፡ ዝና ፡ አሃ

እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
ኃይልህ ፡ የበረታ
ሁሌ ፡ ድል ፡ ነሺ ፡ ነህ
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ
አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ

አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ (፬x)
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ (፪x)

ካልታሰበ ፡ ስፍራ ፡ ከተናቀ ፡ ቦታ
ታናሹ ፡ ሊከብር ፡ ሊታሰብ ፡ በጌታ
ኮተቱን ፡ ሊያስጥለው ፡ ወደላይ ፡ ሊያወጣው
ተራው ፡ ደረሰለት ፡ ከፍታው ፡ ላይ ፡ ሊያወርሰው
ከበረ ፡ ትንሹ ፡ ፈጣን ፡ ነው ፡ ደራሹ (፪x)

አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ግሩም
ሊዘራ ፡ ሲነሳ ፡ አንዳች ፡ አያግደውም
ባለ ፡ ብዙ ፡ ግርማ ፡ አሃ
ባለ ፡ ብዙ ፡ ዝና ፡ አሃ

እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
ኃይልህ ፡ የበረታ
ሁሌ ፡ ድል ፡ ነሺ ፡ ነህ
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ
አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ

አንደኛ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ አንደኛ (፬x)
አንተን ፡ ማን ፡ ሊረታህ (፪x)

የሠማይ ፡ አንደኛ ፡ የምድር ፡ አንደኛ
ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ብቸኛ (፪x)