ተንስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ (Tenes Ante Tewled) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ፋሬስ
(Fares)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 4:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

በውስጥህ ፡ እሳቴን ፡ አቀጣጥላለሁ
የኃጢአትንም ፡ ዱር ፡ ጫካን ፡ እገልጣለሁ
ነበልባሉ ፡ አይጠፋም ፡ ይነዳል ፡ ጨምሮ
ሰሜኑን ፡ ይበላል ፡ ከደቡብ ፡ ጀምሮ

ነውረኛውን ፡ ነገር ፡ ፈጽሞ ፡ እስኪያጠፋ
የነበልባሉን ፡ ኃይል ፡ ማነው ፡ የሚያጠፋ
ብቻ ፡ አንተ ፡ ተቀደስ ፡ ከነውር ፡ ተለይ
ክብሬ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ሊገለጥ ፡ ሊታይ

አዝተነስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ ፡ ተነስ (፪x)
እቃ ፡ ጦርህን ፡ በአግባቡ ፡ ልበስ
ያልታረሰውን ፡ ድንግሉን ፡ ለማረስ
ጫማህን ፡ አጥልቅ ፡ ተነስ
አንተ ፡ ተውልድ ፡ ተነስ

ብዙ ፡ ስራ ፡ አለኝ ፡ በአንተ ፡ የምሰራው
በመጀመሪያ ፡ ግን ፡ ቤቴን ፡ ነው ፡ ማጠራው
እንዳትሆንብኝ ፡ ጥፋት ፡ ከሚያገኘው
ዛሬ ፡ ቀን ፡ እያለ ፡ ተጠንቀቅ ፡ እልሃለሁ

ይሄን ፡ ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ ቢቀናህ ፡ መንገድህ
በምሰራበት ፡ ቀን ፡ ገንዘብ ፡ ትሆናለህ
ሰባራውን ፡ ጠጋኝ ፡ አጋዥ ፡ ትባላለህ
ድል ፡ ነሺ ፡ በመሆን ፡ ደግሞም ፡ ትከብራለህ

አዝተነስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ ፡ ተነስ (፪x)
እቃ ፡ ጦርህን ፡ በአግባቡ ፡ ልበስ
ያልታረሰውን ፡ ድንግሉን ፡ ለማረስ
ጫማህን ፡ አጥልቅ ፡ ተነስ
አንተ ፡ ተውልድ ፡ ተነስ

የተጠራህበት ፡ ጥሪ ፡ ይህ ፡ ነውና
ስራዬን ፡ ልትሰራ ፡ ጊዜው ፡ ቀርቧልና
ቃሌን ፡ በደምብ ፡ ብላ ፡ በአግባቡ ፡ ጸልይ
ሃሳቤ ፡ ይፈጸማል ፡ ያለው ፡ በሰማይ

በምድር ፡ አምባሳደር ፡ ተወካዬ ፡ አንተ ፡ ነህ
ስራዬን ፡ ለመስራት ፡ ከልብ ፡ ከተሰጠህ
መጨረሻው ፡ ደርሷል ፡ የምገለጥበት
ለሁሉም ፡ እንደስራው ፡ ዋጋ ፡ ምከፍልበት

አዝተነስ ፡ አንተ ፡ ትውልድ ፡ ተነስ (፪x)
እቃ ፡ ጦርህን ፡ በአግባቡ ፡ ልበስ
ያልታረሰውን ፡ ድንግሉን ፡ ለማረስ
ጫማህን ፡ አጥልቅ ፡ ተነስ
አንተ ፡ ተውልድ ፡ ተነስ