ለእኔስ ፡ የደላኝ (Lenies Yedelagn) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ፋሬስ
(Fares)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ
በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ
በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው (፪x)

ለእኔስ ፡ የደላኝ ፡ የተመቸኝ
እፎይ ፡ ያልኩበት ፡ ያሳረፈኝ
እንደርሱ ፡ ማነው ፡ የሚደላ
የሚመች ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የሆነኝ ፡ ከለላ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ
በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ
በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው

የምመካበት ፡ መመኪያዬ
ምታመንበት ፡ መታመኚያዬ
የምኮራበት ፡ ጽኑ ፡ ጋሻዬ
ኢየሱሴ ፡ ነው ፡ ማረፊያዬ
ታድያለሁ ፡ ሆኖኛል ፡ ጥላዬ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ
በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ
በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው

ጋሻ ፡ የሆነኝ ፡ ጽኑ ፡ መከታ
ጉልበቴ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እንዳልረታ
በአንዳች ፡ አልሰጋም ፡ አልጨነቅም
ሥጋቴን ፡ ወስዷል ፡ ሥጋት ፡ አላውቅም
እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ በመድሃኒያለም

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ
በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ
በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው