ጉድ ፡ አረገው (Gud Aregew) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ፋሬስ
(Fares)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አበቃለት ፡ ብሎ ፡ ድንጋይ ፡ አትሞበት
ዳግም ፡ እንዳይነሳ ፡ ሁሉን ፡ ዘጋግቶበት
የእርሱ ፡ ነገር ፡ በቃ ፡ ከእንግዲህ ፡ በኋላ
ትንሳኤ ፡ ዓይኖርም ፡ ምንም ፡ መፍትሄ ፡ መላ

ደምድሞ ፡ ቁጭ ፡ ብሎ ፡ የበላይ ፡ ነኝ ፡ ሲል
ድንገት ፡ ሳያስበው ፡ መጣበት ፡ ኃያል
የሞት ፡ መውጊያን ፡ ሽሮ ፡ ጉድ ፡ ሰራው ፡ ጠላቴን
ሕይወት ፡ ታወጀልን ፡ አንሞትም ፡ ሞት
አንሞትም ፡ ሞትን ፤ አንሞትም ፡ ሞትን (፪x)

አዝኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ነው (፪x)
ጉድ ፡ አርጐ ፡ ተነሳ
ሞትን ፡ አሸነፎ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ያንን ፡ ጨካኝ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ሳትናኤልን ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው

የትንሳኤው ፡ ጌታ ፡ ሞትን ፡ አሸንፎ
ኃይላትን ፡ አለቃን ፡ ሥልጣናትን ፡ ገፎ
መቃብር ፡ አልያዘው ፡ ሁሉን ፡ ጥሶ ፡ ወጣ
ለእኛም ፡ ተስፋን ፡ ሰጠን ፡ ደግሞ ፡ እንደሚመጣ

ሰይጣንን ፡ ቀጥቅጦ ፡ ድልን ፡ ስላወጀ
ለፍጥረት ፡ የእርቅ ፡ በር ፡ ድልድዩ ፡ ተበጀ
በኢየሱስ ፡ ለአመንን ፡ አዲስ ፡ ኪዳን ፡ ሆነ
አሮጌ ፡ አዳፋው ፡ ታሪክ ፡ ተከደነ
ታሪክ ፡ ተከደነ ፤ ታሪክ ፡ ተከደነ (፪x)

አዝኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ነው (፪x)
ጉድ ፡ አርጐ ፡ ተነሳ
ሞትን ፡ አሸነፎ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ያንን ፡ ጨካኝ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ሳትናኤልን ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው

ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጽሟል
የእኔም ፡ ስራ ፡ ሁሉ ፡ በእዛ ፡ ሰዓት ፡ አልቋል
የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ዘመን ፡ ለእኔ
ማመኔ ፡ እርግጥ ፡ ነው ፡ በኢየሱስ ፡ መዳኔ

ሞቴን ፡ በሞት ፡ ሽሮ ፡ ሕይወትን ፡ ለሰጠኝ
ዘምርለታለሁ ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ እያለኝ
ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋራ
ስማ ፡ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ከቶ ፡ አንተን ፡ አልፈራ
ከቶ ፡ አንተን ፡ አልፈራ ፤ ከቶ ፡ አንተን ፡ አልፈራ (፪x)

አዝኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ነው (፪x)
ጉድ ፡ አርጐ ፡ ተነሳ
ሞትን ፡ አሸነፎ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ
ያንን ፡ ክፉ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ያንን ፡ ጨካኝ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ሳትናኤልን ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው
ኧረ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ ጉድ ፡ አደረገው