From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ምድራዊ ፡ ሃሳብ ፡ ይዘህ ፡ የምትኖር ፡ እየጫርክ???
እንደሲዖል ፡ ዘንዶ ፡ ደካማ ፡ ምክር ፡ ሆንክ
ዘመን ፡ መጥቶልሃል ፡ ጥሰህ ፡ እንድትወጣ
በእኔ ፡ ክንፍ ፡ ስር ፡ በረህ ፡ ልትቆም ፡ በከፍታ
አዝ፦ ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ ፡ (አሃሃ)
ፋሬስ ፡ (አሄሄሄ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (አሃሃሃ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ አትደበቅ
ቶሎ ፡ አምልጥ ፡ አትቀመጥ
ስፍራህ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ አይደለም
ጥሰህ ፡ ውጣ ፣ ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ ለዘለዓለም
ጽኑ ፡ የአጋዥ ፡ ቀንበር ፡ ተጭኖህ ፡ የጐበጥክ
ማን ፡ ያላቅቀኛል ፡ ብለህ ፡ የተጨነክ
ቅባት ፡ ተለቀቀ ፡ ቀንበርን ፡ የሚሰብር
አንተ ፡ እኮ ፡ ፋሬስ ፡ ነህ ፡ ተነስ ፡ ጌታን ፡ አክብር
አዝ፦ ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ ፡ (አሃሃ)
ፋሬስ ፡ (አሄሄሄ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (አሃሃሃ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ አትደበቅ
ቶሎ ፡ አምልጥ ፡ አትቀመጥ
ስፍራህ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ አይደለም
ጥሰህ ፡ ውጣ ፣ ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ ለዘለዓለም
ሚድያም ፡ አስፈራርቶህ ፡ ተደብቀህ ፡ ያለህ
እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ብለህ ፡ የተማረርህ
ችግር ፡ ተፈራርቆ ፡ ዝለህ ፡ የደካከምክ
መጣስ ፡ የምትችል ፡ ጽኑና ፡ ሓያል ፡ ነህ
አዝ፦ ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ ፡ (አሃሃ)
ፋሬስ ፡ (አሄሄሄ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (አሃሃሃ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ አትደበቅ
ቶሎ ፡ አምልጥ ፡ አትቀመጥ
ስፍራህ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ አይደለም
ጥሰህ ፡ ውጣ ፣ ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ ለዘለዓለም
ሃይማኖትና ፡ ወግ ፡ ባህል ፡ ተጭኖህ
ሰው ፡ ምን ፡ ይለኝ ፡ ይሆን ፡ ብለህ ፡ የፈራህ
ዳግም ፡ ልትወለድ ፡ ጥሰህ ፡ እንድትወጣ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከሰማያት ፡ መጣ
አዝ፦ ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ ፡ (አሃሃ)
ፋሬስ ፡ (አሄሄሄ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (ሆ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ፋሬስ ፡ (አሃሃሃ) ፡ አንተ ፡ ፋሬስ
ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ አትደበቅ
ቶሎ ፡ አምልጥ ፡ አትቀመጥ
ስፍራህ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ አይደለም
ጥሰህ ፡ ውጣ ፣ ጥሰህ ፡ ውጣ ፡ ለዘለዓለም
|