From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተመስገን ፡ ማርቆስ (Temesgen Markos)
|
|
፩ (1)
|
ፋሬስ (Fares)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
|
ቁጥር (Track):
|
፯ (7)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:43
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች (Albums by Temesgen Markos)
|
|
አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፰x)
መገፋት ፡ መሰደዴ ፡ ወደ ፡ ግብጽም ፡ መውረዴ
ወዶኝ ፡ ነው ፡ ያደረገው ፡ አላማ ፡ በእኔ ፡ ስላለው
ወጣሁ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ የበላይ ፡ አደረገኝ
ተሾምኩኝ ፡ ተመረጥኩኝ ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ሆነልኝ (፪x)
ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ሆነልኝ (፬x)
አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፬x)
ሃዘን ፡ ሆነ ፡ መቸገሬ ፡ ኋላ ፡ ግን ፡ ሆነ ፡ ለክብሬ
አለፍኩት ፡ እንደዋዛ ፡ መከራዬ ፡ ረግፎ ፡ እንደጤዛ
ኑሮዬን ፡ እንዲህ ፡ አጣፍጦ ፡ ዘመርኩኝ ፡ ሁሉ ፡ ተረስቶ
ሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ጌታ ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x)
ጌታ ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፬x)
አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፬x)
አይበቃም ፡ እዘምራለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ እኔ ፡ እቀኛለሁ
አምሮልኝ ፡ ሁሉ ፡ ውብ ፡ ሆኗል ፡ መከራዬ ፡ ድልድይ ፡ ሆኖኛል
ተሻገርኩ ፡ ሁሉን ፡ አልፌ ፡ አለሁኝ ፡ ከሞት ፡ ተርፌ
አይቶልኝ ፡ እዚህ ፡ አድርሶኛል ፡ አክብሮ ፡ ያዘምረኛል (፪x)
አክብሮ ፡ ያዘምረኛል (፬x)
አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፰x)
|