በላይ ፡ ነው ፡ ቤቴ (Belay New Bietie) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ፋሬስ
(Fares)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

እወርሳለሁ (፫x) ፡ ሃገሬን ፡ እወርሳለሁ
አያለሁ (፫x) ፡ አምላኬን ፡ አያለሁ

አዝ፦ እኔስ ፡ እውርሳለሁ ፡ ሃገሬን
ደርሼ ፡ አያለሁ ፡ አምላኬን
በምኞት ፡ አልቀርም ፡ ደርሳለሁ
አምላኬ ፡ ይረዳኛል ፡ አምናለሁ
አየዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አየዋለሁ
አየዋለሁ ፡ እርሱን ፡ አየዋለሁ (፪x)

በጉዞ ፡ ላይ ፡ እያለሁ ፡ ብደናቀፍም
ችግርም ፡ መከራ ፡ ቢፈራረቅም
አንድ ፡ ቀን ፡ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ይቀርና
እኔም ፡ እሰዋለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ምሥጋና
አዜማለሁ ፡ ሁሌም ፡ አዜማለሁ
አዜማለሁ ፡ ለጌታ ፡ አዜማለሁ (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ እውርሳለሁ ፡ ሃገሬን
ደርሼ ፡ አያለሁ ፡ አምላኬን
በምኞት ፡ አልቀርም ፡ ደርሳለሁ
አምላኬ ፡ ይረዳኛል ፡ አምናለሁ
አየዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አየዋለሁ
አየዋለሁ ፡ እርሱን ፡ አየዋለሁ (፪x)

ተስፋ ፡ አስቆራጭ ፡ ነገር ፡ በአቋራጭ ፡ ቢነሳም
እምነቴን ፡ ሊያስጥል ፡ በብርቱ ፡ ቢዋጋም
ኢየሱስ ፡ ከጐኔ ፡ ነው ፡ ፍፁም ፡ ላይለየኝ
ቃል ፡ ገብቶልኛል ፡ ጽዮንን ፡ ሊያወርሰኝ
ሊያወርሰኝ ፡ ጌታ ፡ ሊያወርሰኝ
ሊያወርሰኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሊያወርሰኝ (፪x)

አዝ፦ እኔስ ፡ እውርሳለሁ ፡ ሃገሬን
ደርሼ ፡ አያለሁ ፡ አምላኬን
በምኞት ፡ አልቀርም ፡ ደርሳለሁ
አምላኬ ፡ ይረዳኛል ፡ አምናለሁ
አየዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አየዋለሁ
አየዋለሁ ፡ እርሱን ፡ አየዋለሁ (፪x)

ጠላት ፡ ተስፋ ፡ ቁረጥ ፡ እኔ ፡ አምልጫለሁ
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ሲቃ ፡ በኢየሱስ ፡ ድኛለሁ
ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ ሄዳለሁ ፡ አብሬ
ዘለዓለም ፡ እኖራለሁ ፡ በሰማይ ፡ ሃገሬ
በላይ ፡ ነው ፡ ቤቴ ፡ በላይ ፡ ነው
ሰማይ ፡ ነው ፡ ሃገሬ ፡ ሰማይ ፡ ነው (፫x)