አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ (Ante Batredagn Noro) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ፋሬስ
(Fares)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ
አባብዬ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ (፪x)

ስወድቅ ፡ ምታነሳኝ ፡ እየደጋገፍከኝ
አይዞህ ፡ እኔ ፡ አለሁ ፡ እያልክ ፡ ምታጽናናኝ
በሃሩሩ ፡ ጊዜ ፡ ከለላ ፡ የሆንከኝ
ዛሬን ፡ ደርሻለሁ ፡ ጥበቃህ ፡ በዝቶልኝ

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ
አባብዬ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ

ቀኜን ፡ ይዘህ ፡ አንተ ፡ ሁሌ ፡ እየመራኸኝ
ከጐኔ ፡ ማትጠፋ ፡ ጋሻ ፡ እየሆንከኝ
እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ የተንከባከብከኝ
ምከፍልህ ፡ የለኝም ፡ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ
አባብዬ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ
ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ

በዘመኔ ፡ ለአንተ ፡ አዜምልሃለሁ
ከየት ፡ እንዳነሳኸኝ ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ
ጭራሽ ፡ አላየሁም ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
በሰጠኸኝ ፡ ዘመን ፡ ላክብርህ ፡ ጠዋት ፡ ማታ

አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ (የእኔ ፡ ጌታ)
ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ (ወድቄ ፡ ነበረ ፡ ድሮ)
አባብዬ ፡ አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ኖሮ (አባብዬ)
ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ (ጠፍቼ ፡ ነበረ ፡ ድሮ)