አልቆምም (Alqomem) - ተመስገን ፡ ማርቆስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ ማርቆስ
(Temesgen Markos)

Temesgen Markos 1.png


(1)

ፋሬስ
(Fares)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ (2003)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 3:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተመስገን ፡ ማርቆስ ፡ አልበሞች
(Albums by Temesgen Markos)

እጄን ፡ አልሰጥም ፡ ለሚጐትተኝ
ፊት ፡ አልሳይም ፡ ለሚሟገተኝ
የፊቴን ፡ እያየሁ ፡ እዘረጋለሁ
መቆም ፡ አልሻም ፡ በእርሱ ፡ ፈጥናለሁ (፪x)

አዝአልቆምም (፰x)

ገና ፡ እሄዳለሁ ፡ በከፍታ ፡ ላይ
እገሰግሳለሁ ፡ ኋላዬን ፡ ሳላይ
አንዴ ፡ ቀብቶ ፡ ፈቶ ፡ ለቆኛል
በእኔ ፡ የጀመረውን ፡ ገና ፡ ይቀጥላል (፪x)

አዝአልቆምም (፰x)

ጅምሩ ፡ ገና ፡ ታናሽ ፡ ቢሆንም
ጥሶ ፡ ይሄዳል ፡ የሚይዘው ፡ የለም
ቃልኪዳን ፡ አለኝ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር
እርሱን ፡ አክብሬ ፡ እኔም ፡ ልከብር

አዝአልቆምም (፰x)

ታምኜዋለሁ ፡ እንደሚረዳኝ
እስከፍጻሜው ፡ እንደሚመራኝ
እሄዳለሁኝ ፡ ክንዱን ፡ ታምኜ
እወራሳለሁኝ ፡ የበላይ ፡ ሆኜ (፪x)

አዝአልቆምም (፰x)