ተመስገን ፡ ኤልያስ (Temesgen Elias)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

[[ thumbnail ]]የመጎብኛዬ ወራት ሲመጣ ለሚፈሩህ የጽድቅ ፀሐይ ደግሞ ሲወጣ ፀሎቴም ተሰማ ጠላት እየሰማ ዕዳዬ ተከፈለ ከሳሼ የታለ ጉልበቴ በረታ በኢየሱስ ጌታ በል እፈር ጠላቴ እዳዬ ተከፍሏል ከየት ታምጣ ከሳሼ ቀንበሬ ተሰብሯል በነጻነት ልኖር ነጻ አውጥቶኛል ዳግም ላልታሰር ኤፍታ ብሎ ለቆኛል

ክብር ለስሙ ይሁን
ክብር ላዳነኝ ይሁን 
ክብር ለጌታ ይሁን 
ክብር ላየሱስ ይሁን
1.ዝናብም ባይኖር ነፋስም ባላይ
ድል አውጃለሁ ባዶ ተስፋ ላይ 

ደረቁ ምድር ይለመልማል በባዶ ጉድጓድ ዉሃ ይሞላል

ያለቀው ነገር ሞልቶ ይፈሳል 

የተጠማ ሁሉ ጠጥቶ ይረካል

         2.ምንም ቢበዛ የኔ መከራ
ከቶ ቢጎድል የወይራ ሥራ 
ያዳነኝ ጌታ ሀይል ይሆነኛል 
እንደ ዋላ እግሬን ያበረታኝል
ጠባቂዬ የሱስ አቅም ይሆነኛል 
በከፍታ ላይ ያራምደኛል
 3.ያመንኩት ወዳጅ ቢከዳ እንኳን
ቢፈርስ ቢበተን ምድራዊ ድንኳን
የታመንኩ ጌታ ከኔ ጋር ያለው 

ያረጀውን ነገር አዲስ ጀመረው ማይከዳ ወዳጅ ከጎኔ ያለው

የታሪክ መዝገብ አገላበጠው
ያመንኩት የሱስ ከኔ ጋር ያለው
የሞትን አዋጅ ገለባበጠው
     4.ሞቶ ተቀብሮ ቢሸት ነገሬ

አንድም ባይሰማ አስደሳች ወሬ ወድቆ አይቀርም በከንቱ ሞቶ ሕይወት ይዘራል ጌታዬ መጥቶ ትንሣኤ አለ ዛሬም ካባቴ በእግሩ ቆሟል እፈር ጠላቴ


በል እፈር ጠላቴ ብወድቅ እነሳለሁ ቢጨልምብኝ..ም ብርሃን እወጣልሁ

ወደ እግዚአብሔር እመለከ..ታለሁ 

መድኃኒቴን አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ እሱም ይሰማኛል ጽድቅን ያሳየኛል እሱም ያደምጠኛል ዕረፍት ይሰጠኛል።