እግርህን ፡ ልጠብህ (Egrehen Letebeh) - ተመስገን ፡ አበራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተመስገን ፡ አበራ
(Temesgen Abera)


ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የተመስገን ፡ አበራ ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Temesgen Abera)

የምትናፈቅ ፡ የክረምቷ ፡ ፀሀይ
ሙቀቷን ፡ ፍጥረት ፡ ፈልጎ ፡ ሰማይ ፡ ሰማይ ፡ ሲያይ
ብትወጣ ፡ ጭጋጉን ፡ አልፋ
ብትቀር ፡ በደመና ፡ ተውጣ ፡
ህይወት ፡ አይቀርም ፡ ዑደቱ
በቀዝቃዛው ፡ አየር ፡ ዙረቱ
አማራጭ ፡ የሌላት ፡ ነፍሴ ፡ ግን ፡
ሺ ፡ ፀሀይ ፡ ቢወጣ ፡ አይሞቃትም
ውበቷ ፡ ክብሯ ፡ አንተ ፡ ነህ
ከእልፍ ፡ አእላፋት ፡ መካከል ፡ አንድ ፡ እንከን ፡ የሌለህ

ዋላ ፡ ወደ ፡ ውሀ ፡ ምንጭ ፡ እንደምትናፍቅ
ነፍሴ ፡ ገሰገሰች ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አለች

አትሂድ ፡ ከደጄ ፡ ወዳጄ ፡ ቤቴ ፡ ግባ
እግርህን ፡ ልጠብህ ፡ እባክህ ፡ አረፍ ፡ በልና
እንግዶችን ፡ ልሸኝ ፡ ገፍተው ፡ ከልፍኝ ፡ ያራቁህን
ደምቀህ ፡ እንዳትታይ ፡ በምክር ፡ የሚያቀሉህን

አሀሀ ፡ ደጆች ፡ ይከፈቱ
አሀሀ ፡ ፡ የክብር ፡ ንጉስ ፡ ይግባ
አሀሀ ፡ ይህ ፡ የክብር ፡ ንጉስ ፡ ማነው
አሀሀ ፡ የጭፍሮች ፡ አምላክ ፡ እ/ር ፡ ነው

ያላንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ወዳጄ
አረ ፡ እንዴት ፡ ይሆንልኛል ፡ አንተን ፡ ገፍቼ
ኑርና ፡ ልኑር ፡ በህይወት
ስትኖር ፡ ነው ፡ ኖርኩኝ ፡ ማለት
ከኔ ፡ መኖር ፡ ይልቅ ፡ ይሻላል
ሰው ፡ ብቻውን ፡ ምን ፡ ይፈይዳል
ያለ ፡ እኔ ፡ መኖር ፡ የምትችል
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ መኖር ፡ የማልችል
ስለሆንኩ ፡ አትውሰድብኝ
እሳቱን ፡ ከመቅረዙ ፡ ላይ
ዘውትር ፡ ይንደድልኝ

ሰው ፡ እንደሚናኖረው ፡ ለመኖር ፡ ተመሳስዬ
አልቻልኩም ፡ በእንጀራ ፡ ለመዝለቅ ፡ ነፍሴን ፡ አታልዬ
የትም ፡ እንደማልደርስ ፡ ገብቶኛል ፡ በእኔ ፡ እሩጫ
እግሬን ፡ በፈቃድህ ፡ እሰረው ፡ እስከመጨረሻ