ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ (Kurat Kurat Alegn) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)
ርዝመት (Len.): 7:18
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Tekeste Getnet)

ብርቱ ፡ ተብሎ ፡ ታምኖበት ፡ ልብም ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ተጥሎ
አለልኝ ፡ ለእኔ ፡ እያለ ፡ መኖር ፡ ሲመኝ ፡ ተዘልሎ
የተደገፈው ፡ ሸንበቆ ፡ መሆኑን ፡ እንዲያው ፡ ሳያውቀው
ድንገት ፡ ተሰብሮ ፡ ወደቀ ፡ የዚያ ፡ ሰው ፡ መተማመኛው

አኔማ/እኔ ፡ ግን ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ንጉሴን ፡ ሾሜያለሁ
አልፈራ ፡ አልደነግጥ ፡ በክንዱ ፡ እኮራለሁ (፪x)

ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ
እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ
አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፪x)

ዓይኔ ፡ አረፈብህ ፡ ወዳጄ ፡ በምንም ፡ የማትረታ
ወረት ፡ አታውቅም ፡ እንደሰው ፡ በጐ ፡ ነህ ፡ ሁሌ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ዘመናት ፡ ሲፈራረቁ ፡ አልተቀየረም ፡ መውደድህ
ሁሉን ፡ በጆችህ ፡ ይዘሃል ፡ ታስመካለህ ፡ ቢመኩብህ

በልቤ ፡ ሾሜሃለሁ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ፡ ደምቀህ ፡ ታይ
እንዳንተ ፡ የለምና ፡ በምድር ፡ በሰማይ (፪x)

ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ
እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ
አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፪x)

በመከራ ፡ ቀን ፡ ቢጠሩት ፡ አለሁኝ ፡ የሚል ፡ ልብ ፡ ሞልቶ
ግራ ፡ ለገባው ፡ መጠጊያ ፡ ሚደግፍ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ
መተማመኛ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ተፈትኖ ፡ አልፏል ፡ በብ
ደጋግ ፡ እጆቹን ፡ አይተናል ፡ ደካማዎቹን ፡ ሲያግዙ

አለልኝ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ የማይጥል ፡ የማይከዳ
ሰባራን ፡ የሚጠግን ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ በምድረበዳ (፪x)

ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ፡ ብኮራስ ፡ ምናለ
እመካለሁ ፡ እኔስ ፡ ብመካ ፡ ምናለ
አንበሳው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ
ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ሆኖ ፡ የለ
ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤቴን ፡ ሞልቶት ፡ የለ

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ የለምና
በሰማይ ፡ በምድር ፡ አልተገኘምና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይብዛልህ ፡ ነገም ፡ ምሥጋና (፰x)