From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ፡ ቃላትም ፡ አጠረኝ
የሞትን ፡ አዋጅ ፡ ሽሮ ፡ በሕይወት ፡ ኑር ፡ ሲለኝ
ምህረቱ ፡ እንደፀና ፡ የሚያውቀኝ ፡ ያውቀው ፡ የለ
ያ ፡ ክፉ ፡ እንዳይጎዳኝ ፡ ቁጣውን ፡ ከለከለ
እኔማ ፡ ሳሰላስለው ፡ እኔማ ፡ የትናንቱን (፪x)
እኔማ ፡ ምክንያት ፡ ሆነኝ ፡ እኔማ ፡ ፡ ለማመስገን (፪x)
እኔማ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ እኔማ ፡ ዝም ፡ አያሰኘኝ (፪x)
እኔማ ፡ ሀገር ፡ ያውቅ ፡ አይደል ፡ እኔማ ፡ እንደረዳኸኝ (፪x)
የተጠበቁ ፡ ጉድጓዶች ፡ ምንጫቸው ፡ ነጠፈ (፬x)
ያም ፡ ሄደ ፡ እያለፈ ፡ ይሄም ፡ ሄደ ፡ እያለፈ (፬x)
ብቻውን ፡ ህዝቡን ፡ የመራ ፡ በደረቁ ፡ ምድር (፬x)
ምንኛ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኙ ፡ እግዚአብሔር (፬x)
አለኝታዬ (፬x) ፡ መከታዬ (፬x)
ቁምነገር ፡ ተገኘበት ፡ አይጠቅምም ፡ የተባለው
የሰማይ ፡ የምድር ፡ ጌታ ፡ ከሱ ፡ ጋር ፡ አብሮ ፡ ዋለ
በንጉስ ፡ ገበታ ፡ ላይ ፡ ተገኘ ፡ በክብር
ምስኪኑን ፡ የሚያነሳ ፡ ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር
እኔማ ፡ ሳሰላስለው ፡ እኔማ ፡ የትናንቱን (፪x) ፡ ያለፍኩትን (፪x)
እኔማ ፡ ምክንያት ፡ ሆነኝ ፡ እኔማ ፡ ለማመስገን (፪x)
እኔማ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ እኔማ ፡ ዝም ፡ አያሰኘኝ (፪x)
እኔማ ፡ ሀገር ፡ ያውቅ ፡ የለ/እኔማ ፡ እንደረዳኸኝ (፪x)
ሁሉም ፡ ያውቅ ፡ የለ (፪x)
ያሰብኩት ፡ እንዳይሞላ ፡ እንቅፋት ፡ ሲገጥመኝ
ከፊቴ ፡ እየቀደመ ፡ ገለል ፡ አረገልኝ
ማዕበሉ ፡ እንዳያሰጥመኝ ፡ ንፋሱን ፡ ሲገስፀው
አይኔ ፡ አይቷል ፡ በዘመኔ ፡ ፍጥረታት ፡ ሲታዘዘው
እኔማ ፡ ሳሰላስለው ፡ እኔማ ፡ የትናንቱን (፬x) ፡ ያለፍኩትን (፪x)
እኔማ ፡ ምክንያት ፡ ሆነኝ ፡ እኔማ ፡ ለማመስገን (፬x)
እኔማ ፡ እንደሌላ ፡ ሰው ፡ እኔማ ፡ ዝም ፡ አያሰኘኝ (፬x)
እኔማ ፡ ሀገር ፡ ያውቅ ፡ የለ ፡ እኔማ ፡ እንደረዳኸኝ (፬x)
|