From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ይሄዳል ፡ በያምላኩ (፪x)
አልተለቁም ፡ በሚያልፈው ፡ የተመኩ (፪x)
እኛም ፡ ደግሞ ፡ ዘላላም ፡ እንሄዳለን
አናፍርም ፡ አንከሰርም ፡ ጌታን ፡ ታምነን
አምላካችን ፡ መጠጊያችን (፪x)
በመከራ ፡ ረዳታችን (፪x)
ቢነዋወጥ ፡ ምድር ፡ በሞላ (፪x)
ያድነናል ፡ የእኛስ ፡ ከለላ (፪x)
ነገሥታት ፡ ቢቀየሩ ፡ አንዱ ፡ ባንዱ ፡ ቢተካ
እፎይ ፡ ብሎ ፡ ላያድር ፡ ውጥረቱ ፡ ላያበቃ
ዘመን ፡ ያመጣው ፡ ችግር ፡ ትውልድን ፡ ሲያሸብረው
ለፍጥረት ፡ መታመኛ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ለታመነው
አዝ፦ ሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ይሄዳል ፡ በያምላኩ (፪x)
አልተለቁም ፡ በሚያልፈው ፡ የተመኩ (፪x)
እኛም ፡ ደግሞ ፡ ዘላላም ፡ እንሄዳለን
አናፍርም ፡ አንከሰርም ፡ ጌታን ፡ ታምነን
አምላካችን ፡ መጠጊያችን (፪x)
በመከራ ፡ ረዳታችን (፪x)
ቢነዋወጥ ፡ ምድር ፡ በሞላ (፪x)
ያድነናል ፡ የእኛስ ፡ ከለላ (፪x)
ሰው ፡ ባለው ፡ ምን ፡ ቢኮራ ፡ ዓይኑን ፡ ካምላኩ ፡ አንስቶ (፪x)
ቢደገፍ ፡ በሚጠፋው ፡ መገኛውን ፡ ዘንግቶ (፪x)
የቆመ ፡ የመሰለው ፡ እንዳይወድቅ ፡ ይጠንቀቅ (፪x)
ቢናወጥ ፡ ምድር ፡ ሰማይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የሚያዘልቅ (፪x)
ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
|