From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ (ማን ፡ ልበለው ፡ ጌታን
ማን ፡ ልበለው ፡ ኢየሱሴን) X፪
(ከስም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስም ፡ አለው
ለእርሱ ፡ ማይገዛ ፡ እስኪ ፡ ማነው
ሁሉን ፡ በፈቃዱ ፡ የሚያደርገው
አምላኬ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው) X2
(ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ አለፍኩኝ
በምህረቱ ፡ ብዛት ፡ ደግፎኝ
ቢነሳ ፡ ቢነገር ፡ ውለታው
አያልቅም ፡ ካይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው) ፡ X2
አዝ
እንካ ፡ ተንሰራፋ ፡ በልቤ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡
ምን ፡ እኔነት ፡ አለኝ ፡ ሁሉ ፡ ያንተ ፡ አይደል ፡ ወይ
በተቀደሰው ፡ ተራራዬ ፡ ላይ ፡
አንተው ፡ ድመቅበት ፡ ሳይኖርህ ፡ ከልካይ
በሁሉ ፡ ላይ ፡ ሾምኩህ ፡ በሁሉ ፡ ነገር ፡ ላይ
ሁሉም ፡ ይወቅልኝ ፡ (መሆንክን ፡ የበላይ) X2
አንደበቱን ፡ ከፍቶ ፡ ፍጥረት ፡ ያመስግንህ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ (አቻ ፡ አልተገኘልህ) X2
አዝ
(ያፍህ ፡ ቃል ፡ ውድዬ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ አዲስ ፡ ነው
ሳላነሳህ ፡ ውዬ ፡ አላድርም
ከአንተ ፡ ውጪ ፡ እርካታ ፡ የለኝም) X2
አዝ
|