Tekeste Getnet/Negestat Biqeyeru/Bemaderiyaw Lay

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ርዕስ በማደሪያው ላይ አልበም ነገሥታት ቢቀየሩ

አይጓደልም ልማዴ እሰዋለሁኝ ለውዴ ሆነ አልሆነ ነገሩ አባቴ አለ በመንበሩ አይቋረጥም ልማዴ እሰግዳለሁኝ ለውዴ ሞላ አልሞላ ነገሩ እግዚአብሔር አለ በመንበሩ

አዝ በማደሪያው ላይ በዙፋኑ ላይ በመንበሩ ላይ በከፍታው ላይ አለ የሚሰማ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ አለ የሚፈውስ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ

መጣሁ ላመልከው መጣሁ ላደናንቀው መጣሁ ተመስገን ልለው መጣሁ ፍቅሬን ልነግረው ሌላማ መሻት የለኝም ኢየሱስ ይክበርልኝ ሌላማ አምሮት የለኝም ኢየሱስ ይክበርልኝ

አይጓደልም ፡ ልማዴ እሰግዳለሁኝ ፡ ለውዴ ሆነ ፡ አልሆነ ፡ ነገሩ አባቴ ፡ አለ ፡ በመንበሩ አይቋረጥም ፡ ልማዴ እሰግዳለሁኝ ፡ ለውዴ ሞላ ፡ አልሞላ ፡ ነገሩ እግዚአብሔር አለ በመንበሩ

አዝ በማደሪያው ላይ በዙፋኑ ላይ በመንበሩ ላይ በከፍታው ላይ አለ የሚሰማ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ አለ የሚፈውስ የሚያይ አለ የሚረዳ ፡ የሚያይ

ክበር ልበልህ ንገስ ልበልህ ያለኝ ይሄ ነው ይሄ ነው አምልኮን ላንተ አበዛለሁ ያለኝ ይሄ ነው ይሄ ነው ውዳሴን ላንተ አበዛለሁ

ለአስራ ስምንት አመታት መሬት መሬቱን እያየች አቀርቅራ ምትራመድ ጎባጣ ሴት የነበረች በቤተመቅደስ ተገኝታ ልዑልን ስታወድሰው የብዙ ዓመት መከራዋን ከላይዋ አንከባለለው

አዝ በማደሪያው ላይ በዙፋኑ ላይ በመንበሩ ላይ በከፍታው ላይ አለ የሚሰማ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ አለ የሚፈውስ የሚያይ አለ የሚረዳ የሚያይ