በልጅነት (Belejenet) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ነገሥታት ፡ ቢቀየሩ
(Negestat Biqeyeru)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

እኔም ፡ እንዲህ ፡ እንዲህ ፡ ወግ ፡ ደረሰኝ
ከመቅበዝበዝ ፡ እሱ ፡ በቃ ፡ ሲለኝ
ያ ፡ መራራ ፡ ሕይወቴ ፡ ጣፈጠ
በኢየሱሴ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ
አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ
አይቼዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ

አይዞህ ፡ ባየለኝ ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ባይረዳኝ
ማንስ ፡ ሊጎበኘኝ ፡ ማንስ ፡ ሊቀርበኝ
በቃ ፡ ሲል ፡ አበቃ ፡ ያ ፡ ዘመን ፡ አለፈ
ጭጋጉ ፡ ከፊቴ ፡ ይኸው ፡ ተገፈፈ
ለእኔስ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ አድርጎልኛል
ያደላል ፡ ብላችሁ ፡ ማን ፡ ይቀየመኛል
ከናት ፡ ካባት ፡ በላይ ፡ ስለተመቸኝ
እንደሱ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ሁሌ ፡ እላላሁኝ

አዝ፦ ያ ፡ መራራ ፡ ቀን ፡ ያለፈው ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x)
ጭጋጉ ፡ የተገፈፈው ፡ በሱ ፡ ነው (፪x)
ማን ፡ ልበለው ፡ ምን ፡ ልበለው (፪x)
በምን ፡ ቋንቋ ፡ በምን ፡ አንደበት
ይነገራል ፡ የእርሱ ፡ ደግነት

እኔስ ፡ ገና ፡ ገና ፡ በልጅነት
አይቻለሁ ፡ የጌታዬን ፡ ምህረት
ሲርበኝም ፡ ከእጁ ፡ በልቻለሁ
ያንን ፡ ሁሉ ፡ መች ፡ እዘነጋለሁ

አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ (፪x)
አይቼዋለሁ ፡ የሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፪x)
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፪x)

አዝ፦ ያ ፡ መራራ ፡ ቀን ፡ ያለፈው ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x)
ጭጋጉ ፡ የተገፈፈው ፡ በሱ ፡ ነው (፪x)
ማን ፡ ልበለው ፡ ምን ፡ ልበለው (፪x)
በምን ፡ ቋንቋ ፡ በምን ፡ አንደበት
ይነገራል ፡ የእርሱ ፡ ደግነት