ይገርማል (Yigermal) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

እዚህ ፡ እደርሳለሁ ፡ ብዬ ፡ አስቤ ፡ አላውቅም
ከቶ ፡ በእኔ ፡ ጉልበት ፡ የሚቻል ፡ አይደለም ፡ የሚሆን ፡ አይደለም
እርሱ ፡ በፈቃዱ ፡ ይህን ፡ ካደረገው
ከመገረም ፡ ውጪ ፡ ሰዎች ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x)

አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ
ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል
ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ
ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል

አይደንቃችሁም ፡ ወይ ፡ ወገኖች ፡ በሙሉ
ጌታ ፡ ያደረገው ፡ ለእኔ ፡ ለምስኪኑ
እርሱ ፡ በኔ ፡ ሊከብር ፡ መስዋዕቴን ፡ ወዶታል
በደረቁ ፡ አጥንቴ ፡ ዝማሬን ፡ ጨምሯል

አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ
ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል
ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ
ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል

ያዩኝ ፡ ይደነቁ ፡ እዚህ ፡ በመድረሴ
በእርሱ ፡ ሆኖልኛል ፡ አይደለም ፡ በራሴ
የማላገኘውን ፡ ዘመኔን ፡ ብሰራ
ጌታ ፡ አደረሰኝ ፡ እስከ ፡ ጺዮን ፡ ተራራ ፡ ይገርማል

አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ
ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል
ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ
ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል

ከዘመን ፡ ዘመናት ፡ ወደዚህ ፡ አሻግሮ
ቀድሞ ፡ እሱ ፡ ያየውን ፡ በልጁ ፡ ሰውሮ
ዛሬ ፡ ተገለጠ ፡ ፍፃሜው ፡ አማረ
ስንቱን ፡ ጉድ ፡ አሰኘ ፡ ስንቱ ፡ ተገረመ ፡ ይገርማል

አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ
ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል
ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ
ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል

የሚያየኝ ፡ ያክብርህ ፡ ይደነቅብህ
በእኔ ፡ በትንሹ ፡ ስትሰራ ፡ ያየህ
ይናገር ፡ ክብርህን ፡ ምሥጋና ፡ ይጨምር
ያው ፡ ነህ ፡ ለዘላለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ይገርማል

አዝ፦ ይገርማል ፡ ይገርማል ፡ ያረገልኝ
ይገርማል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል
ይደንቃል ፡ ይደንቃል ፡ አሰራሩ
ይደንቃል ፡ ማን ፡ ገምቶ ፡ ያውቃል

አደንቅሃለሁ ፡ አደንቅሃለሁ
ያለኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ከተቀበልከው ፡ አመልክሃለሁ
አመልክሃለሁ ፡ አመልክሃለሁ
ያለኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ከተቀበልከው ፡ አመልክሃለሁ
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ
ቋንቋዬ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ከተቀበልከው ፡ እወድሃለሁ (፪x)