Tekeste Getnet/Mekniyatie Bezu New/Mekniyatie Bezu New

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ርዕስ ምክንያቴ ብዙ ነው Volume 2

    አንደበቴ ከምስጋና በቀር ሌላ አያውቅም
    ይዘምራል ላንተ ክብር ሰለቸኝ አይልም
    ደግነትህ በሕይወቴ እጅግ ስለበዛ
    አሳጣኸኝ ከቶ ምለው ከምሥጋና ሌላ (፪x)

አዝ ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (፪x)

    ከቶ አልሻም በዘመኔ ካንተ ሌላ ለኔ
    ቆርጫለሁ ላልለይህ ኢየሱስ መድህኔ
    ብቻ አንተ ክበር እንጂ ይሁን ደስ እንዳለህ
    አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታዬ ባከብርህ (፪x)

አዝ ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (፪x)

    ልማድህ ነው ከፍ ማድረግ ከብረህ የምታከብር
    ትቢያ አራግፈህ መሸላለም ማብቃት ለቁም ነገር
    ስንቱ አረፈ እፎይ አለ ወዳንተ ሲጠጋ
    አመለጠ ባንተ ጉልበት ከጠላት መንጋጋ (፪x)

አዝ ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (፪x)

     በምስጋና ላይ ምስጋና ገና አበዛለሁ
     ተባረክ ብዬ ሁልጊዜ መቼ እጠግባለሁ (፪x)

በዝማሬ ላይ ዝማሬ ገና አበዛለሁ ተባረክ ብዬ ሁልጊዜ መቼ እጠግባለሁ (፪x)