Tekeste Getnet/Mekniyatie Bezu New/Lesewa Yemesgana Meswaet

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ርዕስ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት ዘማሪ ተከስተ ጌትነት አልበም ምክንያቴ ብዙ ነው


አዝ፦ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት
ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት
ላክብርህ እኔ ደጋግሜ
ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (፪x)


አቤቱ ተደንቄያለሁኝና :ልሰዋ ምሥጋና፦ (፬x)

አቤቱ ተደንቄያለሁኝና :ልሰዋ ምሥጋና፦ (፬x)


ተራራው ከፊቴ እንደሰም ቀለጠ (ምሥጋናዬን) ኤሄ

ቃልህም ሲመጣ ጫካው ተገለጠ (ምሥጋናዬን) ኤሄ

እግሮቼም ጸኑልኝ እንደዋላ እግር (ምሥጋናዬን) ኤሄ

ረዳት ሆነኸኛል አምላኬ ክበር (ምሥጋናዬን) ኤሄ


አዝ፦ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት
ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት
ላክብርህ እኔ ደጋግሜ
ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (፪x)


አቤቱ ተደንቄያለሁኝና :ልሰዋ ምሥጋና፦ (፬x)

ምህረትህ ከሕይወት በእርግጥም ይበልጣል (ምሥጋናዬን) ኤሄ

ደጅ ጥናት የለም በፍጥነት ያነሳል (ምሥጋናዬን) ኤሄ

ድንጋይ ተደርድሮ ሞት ሲጠብቃት (ምሥጋናዬን) ኤሄ

አፍረቷን ሸፍነህ ሰላም ሂጂ አልካት (ምሥጋናዬን) ኤሄ


አዝ፦ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት
ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት
ላክብርህ እኔ ደጋግሜ
ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (፪x)


አቤቱ ተደንቄያለሁኝና :ልሰዋ ምሥጋና፦ (፬x)

ገና ሌሊት ሳለ ንጋት ሳይወጋግን (ምሥጋናዬን) ኤሄ

ምህረትህን ሳስበው ይለኛል አመስግን (ምሥጋናዬን) ኤሄ

ሀሴት አደርጋለሁ በምድር በፊትህ (ምሥጋናዬን) ኤሄ

አንደበቴን ልክፈት ጌታ ላክብርህ (ምሥጋናዬን) ኤሄ


አዝ፦ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት
ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት
ላክብርህ እኔ ደጋግሜ
ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (፪x)


አቤቱ ተደንቄያለሁኝና :ልሰዋ ምሥጋና፦ (፬x)

አቤቱ ተደንቄያለሁኝና :ልሰዋ ምሥጋና፦ (፬x)