ልባርከው (Lebarkew) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

እስኪ ፡ ስሙኝ ፡ አንዴ ፡ ስሙኝ ፡ ልንገራችሁ
ምስኪኑን ፡ ሲያከብር ፡ በዓይናችሁ ፡ ያያችሁ
ኧረ ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ምንስ ፡ ይነገራል
አምላክ ፡ ሥራው ፡ ብዙ ፡ ይህንን ፡ አድርጓል (፪x)

እስኪ ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ አለ (፫x)
እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፫x)

ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው
እርሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው
በእርግጥ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ነው
ልዩ ፡ ነው ፡ እኩያ ፡ የለው

እንደ ፡ አባትም ፡ ሆኖ ፡ ከአባትም ፡ በላይ
ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ
እንዴት ፡ እችላለሁ ፡ በቃላት ፡ ዘርዝሬ
ሥሙን ፡ አከብራለሁ ፡ ይኸው ፡ በዝማሬ

አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው
ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x)

ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ ፡ በርሱ ፡ ተማምኜ
እጅግ ፡ በሚመቸው ፡ ትከሻው ፡ ላይ ፡ ሆኜ
እኔ ፡ አልጨነቅም ፡ ምድር ፡ ቢነዋወጥ
የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ፈፅሞ ፡ አይለዋወጥ

አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው
ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x)

ወጀቡ ፡ ቢነሳ ፡ ከቶ ፡ አያሰጥመኝም
ከኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ ምንም ፡ አይለየኝም
የተናገረኝን ፡ እንደሚፈፅመው
ሁልጊዜ ፡ አምነዋለሁ ፡ አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው

አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው
ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x)

የእግዚአብሔርን ፡ ክንድ ፡ ማን ፡ ይከለክላል
በብርታትስ ፡ በልጦት ፡ ማንስ ፡ ያቆመዋል
ሁሉን ፡ እየረታ ፡ ሲሰራ ፡ የኖረው
እንደ ፡ ትላንትናው ፡ ዛሬም ፡ ጌታ ፡ ያው ፡ ነው

አዝ፦ ልባርከው ፡ ጌታዬን ፡ ልባርከው
ልባርከው ፡ ኢየሱሴን ፡ ልባርከው (፪x)

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ (፫x)
እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ማን ፡ አለ (፫x)

ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ ነህ
አንተስ ፡ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ልዩ ፡ ነህ ፡ እኩያ ፡ የለህ (፪x)