ክበርልኝ (Keberelegn) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክኒያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

፡ ፡ :አዝ፦ ክብርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም
ንገሥልኝ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ አልረካሁም
ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምትወደው
ባቀርብልህ ፡ ጌታ ፡ ምንም ፡ ባልሰለቸው

ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ብለው ፡ ከሚያከብሩህ
እኔን ፡ ከመደብከኝ ፡ ከሚያመሰግኑህ
ጥማቴ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ አክብርሀለሁ
በቀንም ፡ በሌሊትም ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ

 ፡ :አዝ፦ ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም

ሰማይና ፡ ምድር ፡ ክብርህን ፡ ያወራሉ
እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እያሉ
እኔም ፡ ክብርህን ፡ ላውራ ፡ ለትውልድ ፡ ልናገር
የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ክበር

 ፡ ፡ :አዝ፦ ክበርልኝ ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም

ፊትህን ፡ ወደኔ ፡ መልሰሃልና
የአንተ ፡ ወገን ፡ አርገህ ፡ ዋጅተኸኛልና
ከምርጦችህ ፡ ጋራ ፡ እኔም ፡ ተስማምቸ
እስግድልሃለሁ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቸ

 ፡ ፡ :አዝ፦ ክበርልን ፡ ብዬ ፡ ገና ፡ አልጠገብኩም

የምለው ፡ ብዙ ፡ አለኝ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ የማወራው
አምላኬ ፡ ይሔ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የምናገረው
የሚሰማኝና ፡ የሚያየኝ ፡ ያክብርህ
የኔ ፡ ብቻ ፡ አይበቃም ፡ ዘሬም ፡ ይገዛልህ
ብቻ ፡ አንተ ፡ ከወደድከው
ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው