ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና (Gena Alegn Mesgana) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን (፰x)
ዛሬም ፡ ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመሥገን
ሁሌም ፡ ተመሥገን (፪x)

ባህሩን ፡ በኃይል ፡ ከፈልከው (ተመሥገን)
ሕዝብህን ፡ በድል ፡ መራኸው (ተመሥገን)
ጠላት ፡ ጉልበቱ ፡ ተመትቶ (ተመሥገን)
አይተናል ፡ ከባሕር ፡ ሰጥሞ

አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን (፰x)
ዛሬም ፡ ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመሥገን
ሁሌም ፡ ተመሥገን (፪x)

ሃያ ፡ አራት ፡ ሽማግሌዎች ፡ ወድቀው ፡ ክብር ፡ ይሰጡሃል
መላእክት ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ይገባል ፡ ለአንተ ፡ ይሉሃል
እኔም ፡ ባለችኝ ፡ ጊዜ ፡ ላክብርህ ፡ ውዱ ፡ ጌታዬ
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ እላለሁ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ

ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ገና (፬x)

ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና
ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፪x)

አልጠግብ ፡ ባመሰግነው ፡ ተመሥገን ፡ ተመስገን ፡ ብለው
ኢየሱሴ ፡ ለኔ ፡ ያረገው ፡ ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው
አልውልም ፡ ሳላነሳሳው ፡ ሥሙ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
እንደገና ፡ አከብረዋለሁ ፡ ምሥጋናዬ ፡ እስኪ ፡ ይድረሰው

ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ገና (፬x)

ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና
ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፪x)

ገና ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ ገና (፬x)

ገና ፡ ገና ፡ መቼ ፡ ይበቃውና
ገና ፡ ገና ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
ገና ፡ ገና ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና (፫x)