ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል (Feqreh Markognal) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

አዝ፦ ሥምህ ፡ በከንፈሬ ፡ ላይ ፡ ይጣፍጠኛል
ልቤ ፡ ገና ፡ ሲያስብህ ፡ ሃሴት ፡ ያደርጋል
እውነት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ወድጄሃለሁ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል ፡ ተማርኬያለሁ (፯x)

ስላንተ ፡ ማውራት ፡ አይሰለቸኝም
ስምህን ፡ ሳነሳ ፡ ብውል ፡ አልጠግብህም
ውበትህን ፡ ፍፁም ፡ አደንቀዋለሁ
መልካምነትህን ፡ እተርካለሁ (፭x)

አዝ፦ ሥምህ ፡ በከንፈሬ ፡ ላይ ፡ ይጣፍጠኛል
ልቤ ፡ ገና ፡ ሲያስብህ ፡ ሃሴት ፡ ያደርጋል
እውነት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ወድጄሃለሁ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል ፡ ተማርኬያለሁ (፯x)

ተማርኬያለሁ ፡ ስቦኛል ፡ ፍቅርህ
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ጥሎኛል ፡ እንዲገዛልህ
ያንተ ፡ ምርኮኛ ፡ ተረጂ ፡ ሆኛለሁ
እንደወደድክ ፡ አርገኝ ፡ ተማርኬያለሁ (፭x)

አዝ፦ ሥምህ ፡ በከንፈሬ ፡ ላይ ፡ ይጣፍጠኛል
ልቤ ፡ ገና ፡ ሲያስብህ ፡ ሃሴት ፡ ያደርጋል
እውነት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ወድጄሃለሁ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል ፡ ተማርኬያለሁ (፯x)

በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ነፍሱን ፡ ለኔ ፡ ሰጥቶ
ታደገ ፡ ጌታዬ ፡ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ሞቶ
ከዚህ ፡ ሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ ለማንም ፡ የለው
የጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነው (፭x)

አዝ፦ ሥምህ ፡ በከንፈሬ ፡ ላይ ፡ ይጣፍጠኛል
ልቤ ፡ ገና ፡ ሲያስብህ ፡ ሀሴት ፡ ያደርጋል
እውነት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ወድጄሃለሁ
ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል ፡ ተማርኬያለሁ (፯x)

ተማርኬያለሁ (፰x)
ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነው (፰x)