እጠብቃለሁ (Etebeqalehu) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

አዝ:- እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ፡ ከአንተ ፡ የት ፡ እሄዳለሁ
እጠብቃለሁ ፡ ዛሬም ፡ እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ፡ ከአንተ ፡ የት ፡ እሄዳለሁ (፪x)

በለስ ፡ እንኳን ፡ ባያፈራ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ
ወይን ፡ ፍሬ ፡ ባይጐመራ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ
ከብቶች ፡ በጋጡት ፡ ባይኖሩ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ
እርሾች ፡ ምግብን ፡ ባይሰጡ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ

አዝ:- እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ፡ ከአንተ ፡ የት ፡ እሄዳለሁ
እጠብቃለሁ ፡ ዛሬም ፡ እጠብቃለሁ
እጠብቃለሁ ፡ ከአንተ ፡ የት ፡ እሄዳለሁ

አንተ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ
አንተ ፡ ጊዜ ፡ የማይልውጥህ
አንተ ፡ ዘግይተህ ፡ ተነስተህ
አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ትደርሳለህ (፪x)

ያኔ ፡ በሸለቆ ፡ ደግሞም ፡ በተራራ (፪x)
ወየው ፡ ጠፋሁ ፡ ብዬ ፡ አምላኬን ፡ ስጣራ (፪x)
በጨነቀ ፡ ጊዜ ፡ ተገልጦ ፡ አይቻለሁ
ስጋት ፡ አይገባኝም ፡ ዛሬም ፡ አምነዋለሁ ፣ ዛሬም ፡ አምነዋለሁ (፪x)

ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ ይረዳኛል (፪x)
ያግዘኛል ፡ አምናለሁ ፡ ያግዘኛል (፪x)
ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ ይረዳኛል (፪x)
ያግዘኛል ፡ አምናለሁ ፡ ያግዘኛል (፪x)

አንገቴን ፡ አልደፋም ፡ አጋዥ ፡ እንደሌለው
እንደ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ለምን ፡ መቆዘሜ ፡ ሃሳቢ ፡ እንደሌለው
የነአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ዛሬም ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)

ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ ይረዳኛል (፪x)
ያግዘኛል ፡ አምናለሁ ፡ ያግዘኛል (፪x)

አንተ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ
አንተ ፡ ጊዜ ፡ የማይልወጥህ
አንተ ፡ ዘግይተህ ፡ ተነስተህ
አንተ ፡ ቀድመህ ፡ ትደርሳለህ (፪x)