አይቼዋለሁ (Ayechiewalehu) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Lyrics.jpg


(2)

ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
(Mekniyatie Bezu New)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 7:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

እኔም ፡ እንዲህ ፡ እንዲህ ፡ ወግ ፡ ደረሰኝ
ከመቅበዝበዝ ፡ እርሱ ፡ በቃህ ፡ ሲለኝ
ያ ፡ መራራ ፡ ሕይወቴ ፡ ጣፈጠ
በኢየሱሴ ፡ ታሪክ ፡ ተለወጠ

አዝ፦ አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ
አይቼዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)

እኔስ ፡ ገና ፡ ገና ፡ በልጅነት
አይቻለሁ ፡ የጌታዬን ፡ ምህረት
ሲርበኝም ፡ ከእጁ ፡ በልቻለሁ
ያንን ፡ ሁሉ ፡ መች ፡ እዘነጋለሁ

አዝ፦ አይቼዋለሁ ፡ ጌታን ፡ አይቼዋለሁ
አይቼዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ጌታን ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ ኢየሱሴን ፡ ለኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)

ማን ፡ ልበለው ፡ ምን ፡ ለበለው (፪x)
በምን ፡ ቋንቋ ፡ በምን ፡ አንደበት
ይነገራል ፡ የርሱ ፡ ደግነት (፪x)

አይቼዋለሁ ፡ አይቼዋለሁ
እኔ ፡ አውቀዋለሁ ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፫x)