Tekeste Getnet/Mejemeriya/Yilegnal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘምር ፡ ዘምር ፡ ይለኛል ፡ ቀኝህ ፡ ስለደገፈኝ

ድቅድቁ ፡ ሌሊት ፡ አለፈ ፡ የሚነጋ ፡ ያልመሰለኝ

ባለውለታዬ ፡ ሆይ ፡ ብቸኛ ፡ መመኪያዬ

እውነትም ፡ የጭንቅ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ ነበረ ፡ ምርጫዬ


ያ ፡ የጨለማ ፡ ዘመን ፡ አለፈ ፡ አበቃ

ምርኮ ፡ መጣልኝ ፡ እየጐረፈ ፡ ፡ አበቃ

የሀዘን ፡ ሸማ ፡ ከላዬ ፡ ወልቋል ፡ አበቃ

ሰላሙ ፡ ልቤን ፡ አጥለቅልቆታል ፡ አበቃ


በቃ ፡ ሲለዉ ፡ አበቃ ፡ ገደብን ፡ አበጀዉ

ያስጨነቀኝን ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ለወጠዉ

ኤፍታህ ፡ ብሎ ፡ ለቆኛል ፡ በደስታ ፡ ልቀኝለት ፡

ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ፡ ተው ፡ ባይ ፡ ከልካይ ፡ የለበት

ይብዛልህ ፡ ክብር ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና የመኖሬ ምስጢር ጌታ አንተ ነህና

ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ምስጋና የመቆሜ ምስጢር ጌታ አንተ ነህና

ዞር ፡ ስል ፡ ወደኋላ ፡ ታሪኬ ፡ ሚናገረው

ባወራ ፡ የማላፍርበት ፡ ረዳቴ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ

ለዚህ ፡ ነዉ ፡ መታመኔ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ሚያዘምረኝ

በሚያስፈራው ፡ ወጀብ ፡ ላይ ፡ ሰማሁት ፡ አለሁህ ፡ ሲለኝ


ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ ልውጣ ፡ ከጥሻው ፡ ፡ አበቃ

በገናን ፡ ላንሳ ፡ ስለውለታው ፡ ፡ አበቃ

ድምጼ ፡ ይሰማ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ ፡ ፡ አበቃ

ለሥሙ ፡ ማጠን ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ስራ ፡ ፡ አበቃ


በቃ ፡ ሲለዉ ፡ አበቃ ፡ ገደብን ፡ አበጀዉ

ያሰጨነቀኝን ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ለወጠዉ

ኤፍታ ፡ ብሎ ፡ ለቆኛል ፡ በደስታ ፡ ልቀኝለት ፡

ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ፡ ተው ፡ ባይ ፡ ከልካይ ፡ የለበት ፡ ፡


ይብዛልህ ፡ ክብር ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና የመኖሬ ምስጢር ጌታ አንተ ነህና


ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ምስጋና የመቆሜ ፡ ሚስጢር ፡ ጌታ ፡አንተ ፡ ነህና ፡