From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ፍቅር ፡ የጎደለበት ፡ ባግባቡ ፡ እንኳን ፡ ያልኖረ
አይዞ ፡ ባይ ፡ ወገን ፡ የሌለው ፡ ብቸኛ ፡ የነበረ
ያለበት ፡ ድረስ ፡ መተህ ፡ ወድሃለው ፡ ስትለው
ልቡን ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር ፡ ምንስ ፡ ሌላ ፡ አማራጭ ፡ አለው
መመኪያዬ (X3) አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (X2)
ላፍታ ፡ ሳትለየኝ ፡ በድካም ፡ ሆነ ፡ በብርታት
ስንት ፡ ግዜ ፡ ረዳኀኝ ፡ ባሳለፍኳቸው ፡ አመታት
ልቤን ፡ ኩራት ፡ አለው ፡ ዘንድሮም ፡ ተመካብህ
የማትለዋወጥ ፡ የህይወቴ ፡ ዋስትና ፡ ነህ
የሁሌ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ የሁሌ
አፍቃሪ ፡ ወረት ፡ የለብህ ፡ ውዴ ፡ ልበልህ ፡ እንዳመሌ
ማይዘነጋ ፡ ነው ፡ አይጠፋም ፡ ከሃሳቤ
ሁሌ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ ፍቅርህ ፡ ታትሟል ፡ በልቤ
ብዙ ፡ ወጀብ ፡ አልፎ ፡ ትኩሳቱ ፡ እንደው ፡ አይበርድም
ዛሬም ፡ አንተኑ ፡ ይለኛል ፡ አይለውጥህም ፡ በማንም
የሁሌ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ የሁሌ
አፍቃሪ ፡ ወረት ፡ የለብህ ፡ ውዴ ፡ ልበልህ ፡ እንዳመሌ
ማይዘነጋ ፡ ነው ፡ አይጠፋም ፡ ከሃሳቤ
ሁሌ ፡ ድቅን ፡ ይልብኛል ፡ ፍቅርህ ፡ ታትሟል ፡ በልቤ
ብዙ ፡ ወጀብ ፡ አልፎ ፡ ትኩሳቱ ፡ እንደው ፡ አይበርድም
ዛሬም ፡ አንተኑ ፡ ይለኛል ፡ አይለውጥህም ፡ በማንም
የሁሌ ፡ ነህ ፡ የሁሌ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ የሁሌ
አፍቃሪ ፡ ወረት ፡ የለብህ ፡ ውዴ ፡ ልበልህ ፡ እንዳመሌ
|