Tekeste Getnet/Mejemeriya/Yastaweqebegnal

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
   Lyrics
   ዘማሪ=ተከስተ  


   ምነው ይበጃል ውይ ዝም ማለት
   ምነው ይሄ ሁሉ ተደርጐለት
   ምነው ሌላ ቃላት በተገኘ
   ምነው ልቤ ቢልህ እንደተመኘ
    ያስታውቅብኛል የተገለጠ ነው 
    የሱን መልካምነት አልችልም ልደብቀው 
    አቅም እየሆነ 
    ብርታት እየሆነ 
    እዚህ እንዳደረሰኝ
    ምልክት ለሚሻ እኔን ይመልከተኝ
   ይሄው ምሥጋናዬ x፪
   መውደዴን ማወራበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ 
   ይሄው ዝማሬዬ ይሄው እልልታዬ ፍቅሬን                                                        የምገልጥበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ  


    ቸርነትህ ብዙ ብዙ 
    በጐነትህ ብዙ ብዙ
    ስትረዳ ብዙ ብዙ
    ስትመረ ብዙ ብዙ


    / ይወራ ይነገር 
      ለኔማ ያረከው ነገር /፪
     1)ምን መላ አለው እየተባለ
      ከሰው ተራ የተገለለ 
      ቸርነትን ከአንተ አግኝቶ 
      ያካብርሀል በፊትህ ቆሞ
      ቸርነትህን ላውራው ላውራው
      ሰው የሆንኩት በአንተ ነው በአንተ ነው
      በጎነትህን ላውራው ላውራው 
      ሰው የሆንኩት በአንተ ነው በአንተ ነው
              / ይወራ ይነገር 
               ለኔማ ያረከው ነገር/፪
    ያስታውቅብኛል የተገለጠ ነው 
    የሱን መልካምነት አልችልም ልደብቀው 
      አቅም እየሆነ
      ብርታት እየሆነ 
      ሞገስ እየሆነ
            እዚህ እንዳደረሰኝ 
            ምልክት ለሚሻ እኔን 
    ይመልከተኝ
    ይሄው ምሥጋናዬ/፪  
   ፍቅሬን የምገልጥበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ
    ይሄው ዝማሬዬ/፪ 
   መውደዴን ማወራበት አንድ ያለኝ ስጦታዬ}}