Tekeste Getnet/Mejemeriya/Wetrom
ዘማሪ ተከስተ ጌትነት
ርዕስ ወትሮም
አልበም መጀመሪያ
እኔ እንደው ልማዴ ነው ሳይነጋ መዘመር
እኔ እንደው ልማድ አለኝ ችግር ፊት መዘመር
ስላንተ ሲወራ ደስ ደስ ይለኝ ጀመር
ሁሉ ደህና ነው ስል ደህና ሆኖ ቀረ
አስፈሪው ተራራ ሆነ እንዳልነበረ
ድሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ
ወትሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ
ልበልህ ጌታዬ /3×/
ልበልህ ንጉሴ /3×/
ድሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ
ወትሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ
የዕለቱን መስዋዕት ከእኔ የሚሻው
ላሳርግለት ያውድ መዓዛው
አያፍርም ፊቴ እርሱ ጋ ደርሶ
ይለውጠዋል ሁሉን አድሶ
ጥያቄ ኖሮ ያልተመለሰ
መዘመር አልተው ፍቅሬም አልቀነሰ
ማጠኛውን ስጡኝ የተራዬን ልበል
እኔ ጋር ደርሶ አምልኮ አይጓደል
ድሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ
ወትሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ
ላስተዋለውማ ተፈጥሮም ያወራል
ሊነጋጋ ሲቀርብ እጅግ ይጨልማል
ምልክት ነበር ድቅድቅ ማለቱ
የመጎብኛዬ ደረሰ ሰዓቱ
ድሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ
ወትሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ
ልበልህ ጌታዬ /3×/
ልበልህ ንጉሴ /3×/
ድሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት መተህማ አላሳንስህ
ወትሮም የበላይ ነህ
ክብር ነው መገኛህ
እኔ ቤት ሲሆን ሲሆን አልቆጥብብህ