መበርቻዬ (Meberchayie) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 6.jpg


(6)

መጀመሪያ
(Mejemeriya)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

የነጠፈው ፡ ሸለቆ፡ ምንም ውኃ ፡ የለለበት፡
ስንቱ ፡ ጠጥቶት ፡ ረካ ፡ ተዓምር ፡ ሰሪው ፡ ሲገኝበት ፡ እሬት ሬት ያለው ሕይወት ፡ ሲቀምሱት ፡ ጣፈጠ ፡
አንተ ፡ እጅ ፡ ላይ ፡ ስገባ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ተለወጠ ፡

ስደክም ፡ እያበረታኝ ፡ ሳዝንም እያጽናናኝ ፡(X2) ፡
እግዚአብሔር ፡ እኔ አለው እያለ ፡ ሳይለየኝ ከእኔ ጋራ ዋለ ፡
እግዚአብሔር ፡ በቂ ነኝ እንዳለ ፡ ክረምት ፡ በጋ ፡ ከእኔ ጋራ ፡ ዋለ ፡

መበርቻ ፡ መበርቻዬ ፡ መበርቻ ፡ መበርቻዬ ፡
መበርቻዬ ፡ (X3) ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡
መጽናኛዬ ፡(X3) ፡ እየሱስ ጌታዬ ፡

ብራድ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ትኩስ ፡ እንድሁ ፡ ለብ ፡ ያለ ፡
ለጌታው ፡ መኖር ፡ እያቃተው ፡ ህይወቱ ፡ የሰለለ ፡
የፍቅሩ ፡ ጥልቀት ፡ እንጂ ፡እስካሁን ፡ መሰንበቱ ፡
እንደዝያማ ፡ ባይሆን ፡ ኖሮ ፡ ቁርጥ ፡ ነበር ፡ መጠፋቱ ፡

ስደክም ፡ እያበረታኝ ፡ ሳዝንም እያጽናናኝ ፡(X2) ፡
እግዚአብሔር ፡ እኔ አለው እያለ ፡ ሳይለየኝ ከእኔ ጋራ ዋለ ፡
እግዚአብሔር ፡ በቂ ፡ ነኝ ፡ እንዳለ ፡ ክረምት ፡ በጋ ፡ ከእኔ ጋራ ፡ ዋለ ፡