መባረክ (Mebarek) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 6.jpg


(6)

መጀመሪያ
(Mejemeriya)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ያረፌ ፡ ሰዉ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ የተመካ ፡
ከቶ ፡ አይሰጋም ፡ አያስፈራው ፡ ክረምት ፡ በጋ ፡ አያሰጋ ፡

መቸ ፡ ፈራ ፡ ልቤ ፡ አልደነገጠም ፡ ያባቶች ፡ አምላክ ፡ መች ፡ ተለወጠ ፡
ክዳኑ ፡ ጽኑ ፡ አይታጠፍም ፡ እንደልማዴ ፡ አልኩኝ ፡ እርፍ ፡

በማለዳ ፡ በምሽቱ ፡ እዘምራለሁ ፡ በቸርነቱ ፡
ባንደበተ ፡ ሞልቷል ፡ ምስጋና ፡ በህይወት ፡ መኖረ ፡ በርሱ ፡ ነውና ፡

አላልፈውም ፡ ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ነበረ ፡ የሞቱንም ፡ አዋጅ ፡ ጌታዬ ፡ ሰባበረ ፡
ታምር ፡ በስቶብኛል ፡ የማወራው አለኝ ፡
መባረክ ፡ አይደክመውም ፡ መዘመር ፡ አይደክመኝ ፡

አገር ፡ ሰላም ፡ ሁሉ ደና ነው ፡ ነገሬ ፡ ሁሉ ፡ በርሱ ፡ ነው ፡ ያለው ፡
ተዘልዬ ፡ በጥበቃው ፡ ስር ፡ እኖራለው ፡ ሳልሸባበር ፡

አላልፈውም ፡ ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ነበረ ፡ የሞቱንም ፡ አዋጅ ፡ ጌታዬ ፡ ሰባበረ ፡
ታምር ፡ በስቶብኛል ፡ የማወራው አለኝ ፡
መባረክ ፡ አይደክመውም ፡ መዘመር ፡ አይደክመኝ ፡