እንደገና (Endegena) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 6.jpg


(6)

መጀመሪያ
(Mejemeriya)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ውለታውን ፡ ያልረሳ ፡ ከነ ፡ ጋር ፡ ምስጋና ፡ ያንሳ
በጎነቱን ያልረሳ ፡ ያልረሳ ፡ ከነ ፡ ጋር ፡ ምስጋና ፡ ያንሳ
ቸርነቱን ያልረሳ ፡ ያልረሳ ፡ ከነ ፡ ጋር ፡ ምስጋና ፡ ያንሳ

ያ ፡ ለምፃም ፡ ፈርሳዊ ፡ ንጉስን ፡ ቤቱ ፡ ጠርቶ ፡
እስራኤል ፡ እንዳለለማድ ፡ ውሃ ፡ እንኳን ፡ ማቅረቡን ትቶ ፡
ከሩቅ ፡ ሰምታ ፡ የመጣችው ፡ ፍቅሩ ፡ እንደእብድ ፡ ያደረጋት ፡
አብዝታ ፡ ክብር ፡ ሰጠችው ፡ ምንም ፡ ነገር ሳይበግራት ፡

ሽቶውን ፡ ነሰነሰችው ፡ መዓዛው ፡ ቤቱን ፡ ሞላ ፡
አበዛች ፡ አልተወችው ፡ ቁጭብሎ ፡ ይዛ ፡ የሚያሰላት ፡
ተዋት ፡ ብሎ ተዛዝ ሰጠ ፡ የምታድርገውን ሁሉ ፡
ብዙ ፡ ይተውለታል ፡ ብዙ ፡ የወደደ ፡ ፈቅዶ ፡

ተዋት ፡ እስኪ ፡ ተዋት ፡ ትዘምርለት ፡ ተዋት ፡
እሷ ፡ ናት ፡ እምታውቀው ፡ ምን ፡ እንደ ፡ ተደረገላት ፡

እንደገና ፡ መቶልናልና ፡ ለሱ ፡ ክብር ፡ ይብዛ ፡ ምስጋና ፡ (X4)

ያለፈህን ፡ የሚያወድስ ፡ እሱማ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ብሎ ፡
ድንገት ፡ ቀኑ ፡ ስከዳ ፡ ብያይህም ፡ ከሰው ፡ ነጥሎ ፡
የዳንክ ፡ በተሰቀለው ፡ ያነጻ ፡ ደሙ ፡ ነውና ፡
በሆነው ፡ አትጨናነቅ ፡ ያንግዘ ፡ ወዶሃልና ፡

ታድያ ፡ ሚከስ ፡ ማነው ፡ ኑር ፡ በሰላም ፡ ሳትሰጋ ፡
ድርድር ፡ ያለው ፡ ይቅረብ ፡ አለ ፡ ፀሎት ፡ ጠበቃ ፡
ያነ ፡ አለም ፡ ሳይፈጠር ፡ ገና ፡ ገና ፡ ከጥንቱ ፡
ነውር ፡ አልባ ፡ አድርጎሃል ፡ አቁሞሃል ፡ በፊቱ ፡

ተውት ፡ እስኪ ፡ ተውት ፡ ይዘምር ፡ እስኪ ፡ ተውት ፡
እሱኮ ፡ ነው ፡ የሚያውቀው ፡ ምን ፡ እንደተደረገለት ፡

እንደገና ፡ መቶልናልና ፡ ለሱ ፡ ክብር ፡ ይብዛ ፡ ምስጋና ፡ (X4)