እንዳለፈው (Endalefew) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Tekeste Getnet 6.jpg


(6)

መጀመሪያ
(Mejemeriya)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፩ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 3:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተከስተ ፡ ጌትነት ፡ አልበሞች
(Albums by Tekeste Getnet)

ያስፈራራ ነበር ጨለማው
እግዚኦ እግዚኦ ያሰኘ ነው
ሁኔታ ሲመጣ እየከፋ
 ለጥቂት ቀን ሚሆን እምነት ጠፉ
ወየሁ ጠፋሁኝ ብዬ ያለቀልኝ ሲመስለኝ
በድቅድቁ ለሊት ላይ ጎኔ ቆሞ አበረታኝ
ሁን ሲል የሚሆንለት ቃል አውጥቶ ሂድ አለው
የማያልፍ የመሰለኝ ያም አለፈ እንዳለፈው

 ያም አለፈ እንዳለፈው ያም አለፈ እንዳለፈው
 ያም አለፈ እንዳለፈው ያም አለፈ እንዳለፈው

ሆ ብሎ ወጥቶ ነበር ጦሩን አሰባስቦ
አይዞህ የሚል ባይኖር መልካም ቀን አስቦ
እንደሰው አይደለም ብለን ያዜምንለት
 እንደገና አቆመን በብዙ በረከት

ምን አይነት ነገር ነው የወረደው
የብዙሃኖችን ነው ልብ ያራደው
የሚያተርፍ አይመስል አመጣጡ
ብዙ ሀያላኖች እጅ ሰጡ
እኔም ያው ሰው ነኝ እና ያለቀልኝ ሲመስለኝ
በድቅድቁ ለሊት ላይ ጎኔ ቆሞ አበረታኝ
ሁን ሲል የሚሆንለት ቃል አውጥቶ ሂድ አለው
የማያልፍ የመሰለኝ ያም አለፈ እንዳለፈው

 ያም አለፈ እንዳለፈው ያም አለፈ እንዳለፈው
 ያም አለፈ እንዳለፈው ያም አለፈ እንዳለፈው