From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ጩህ ጩህ ይለኛል የማደርገው ሳጣ
መልካምነትህ ፍቅርህ እየመጣ
መጮህ ያምረኛል ቃላት እያጠረኝ
ያ ደግነትህ ፍቅርህ ትዝ እያለኝ
ጩህ ጩህ ይለኛል መዳኔን ሳስበው
ያደረክልኝ ከቃላት በላይ ነው
ውስጤን የፈነቀለው የምስጋናዬ ዜማ
ያርግ ወደ ማደርያህ ጣፋጭ ሆኖ ይሰማ
ይታይ እንደረዳኽኝ ሀገር ሁሉ ይወቀው
እንዴት ችሎ ዝም ይላል እንደኔ የረዳኽው (X6)
ምህረቱን ዓይና ማዳኑን ዓይና
ፍቅሩንም ዓይና ትእግስቱን ዓይና
ተነሳሳ ልቤ ለምስጋና ዘምር ዘምር አለኝ እንደገና
ቁስለኛው/ እስረኛው ተነስቶ ቆሟልና (X4)
ሜልኮል ትናቀኝ እንደለመደባት
ተፈቶ ማምለክ መቼም አይሆንላት
ባለታሪክ ነኝ እግዜር የረዳኝ
በደግ እጆቹ ድግፍ ያረገኝ
ውስጤን የፈነቀለው የምስጋናዬ ዜማ
ያርግ ወደ ማዳርያህ ጣፈጭ ሆኖ ይሳማ
ይታይ እንደረዳኸኝ ሀገር ሁሉ ይወቀው
እንዴት ችለው ዝም ይላል እንደኔው የረደኸው
ያባቶች አምላክ ነው የረዳኝ
ከድቅድቅ ጨለማ ያወጣኝ
የዳዊት አምላክ ነው የረዳኝ
ከትብያ ካመድ ላይ ያነሳኝ
ምህረቱን ዓይና
ማዳኑን ዓይና
ፍቅሩንም ዓይና
ትዕግሥቱን ዓይና
ተነሳሳ ልቤ ለምስጋና
ዘምር ዘምር አለኝ እንደገና
ቁስለኛው ተነስቶ ቆሟልና (4x)
|